2 ሳሙኤል 19:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ሜምፌቡስቴም አለ፥ “ጌታዬ፥ ንጉሥ፥ አገልጋዬ አታለለኝ፥ እኔ ባሪያህ አንካሳ ነኝና፦ ከንጉሡ ጋር እሄድ ዘንድ አህያዬን ጫንልኝ፤ እኔም እቀመጥበታለሁ አልሁት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 እርሱም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ ሽባ በመሆኔ፣ ‘ከንጉሡ ጋራ መሄድ እንድችል አህያዬ ይጫንልኝና ልቀመጥበት’ ብዬ ነበር፤ ይሁን እንጂ አገልጋዬ ሲባ አታለለኝ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 እርሱም ንጉሡን ለመቀበል ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “መፊቦሼት፥ አብረኸኝ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 መፊቦሼትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፥ እንደምታውቀው እኔ ሽባ ነኝ፤ ከአንተ ጋር ለመሄድ ፈልጌ አገልጋዬን ‘በቅሎዬን ጫንልኝ’ ብለው ከድቶኝ ሄደ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 እርሱም መልሶ አለ፦ ጌታዬ፥ ንጉሥ ሆይ፥ ባሪያዬ አታለለኝ፥ እኔ ባሪያህ አንካሳ ነኝና፦ ከንጉሥ ጋር እሄድ ዘንድ የምቀመጥበትን አህያ ልጫን አልሁት። 参见章节 |