Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 19:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እር​ሱም ንጉ​ሡን አለው፥ “ጌታዬ! ኀጢ​አ​ቴን አት​ቍ​ጠ​ር​ብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጣህ ቀን ባሪ​ያህ የበ​ደ​ል​ሁ​ህን አታ​ስ​ብ​ብኝ፤ ጌታዬ ንጉ​ሡም በል​ብህ አታ​ኑ​ር​ብኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ በደሌን አይቍጠርብኝ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከኢየሩሳሌም በወጣህባት ዕለት የፈጸምሁትን ስሕተት እርሳው፤ ከአእምሮህም አውጣው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የንጉሡን ቤተሰብ ለማምጣትና እርሱ የሚፈልገውንም ሁሉ ለማድረግ ዮርዳኖስን ተሻገሩ። የጌራ ልጅ ሳሚ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ በንጉሡም ፊት ተደፍቶ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “ንጉሥ ሆይ! ከኢየሩሳሌም ወጥተህ በሄድክበት ቀን ያደረግኹትን በደል እባክህ ይቅር በለኝ፤ ቂም በቀልም አትያዝብኝ፤ ዳግመኛም ስለ እርሱ አታስብ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ንጉሡንም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ኃጢአቴን አትቍጠርብኝ፥ ጌታዬ ንጉሡ፥ ከኢየሩሳሌም በወጣህ ቀነ ባሪያህ የበደልሁህን አታስብብኝ፥ ንጉሡም በልቡ አያኑረው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 19:19
17 交叉引用  

ወን​ድ​ም​ዋም አቤ​ሴ​ሎም፥ “ወን​ድ​ምሽ አም​ኖን ከአ​ንቺ ጋር ነበ​ርን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፤ ወን​ድ​ምሽ ነውና፤ ይህን ነገር ትና​ገሪ ዘንድ በል​ብሽ አታ​ስቢ” አላት። ትዕ​ማ​ርም በወ​ን​ድ​ምዋ በአ​ቤ​ሴ​ሎም ቤት መበ​ለት ሆና ተቀ​መ​ጠች።


አሁ​ንም የሞተ አም​ኖን ብቻ ነው እንጂ የን​ጉሥ ልጆች ሁሉ ሞቱ ብሎ ጌታዬ ንጉሡ ይህን ነገር በልቡ አያ​ስብ።”


ንጉ​ሡ​ንም የማ​ሻ​ገር ሥራ ሠሩ። የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ ሰብእ ያነሡ ዘንድ፥ በፊ​ቱም የቀና ሥራን ይሠሩ ዘንድ ወደ ማዶ ተሻ​ገሩ። ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ከተ​ሻ​ገረ በኋላ የጌራ ልጅ ሳሚ በን​ጉሡ ፊት፦ በግ​ን​ባሩ ወደቀ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ሰ​ንቆ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ዐሥር አው​ታ​ርም ባለው በገና ዘም​ሩ​ለት።


ከግ​ብፅ የወ​ይ​ንን ግንድ አመ​ጣህ፤ አሕ​ዛ​ብን አባ​ረ​ርህ፥ እር​ስ​ዋ​ንም ተከ​ልህ።


ትዕ​ግ​ሥት ታላ​ቁን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና የገዢ ቍጣ የተ​ነ​ሣ​ብህ እንደ ሆነ ስፍ​ራ​ህን አት​ል​ቀቅ።


መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።


እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕወቅ ብሎ አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያው​ቁ​ኛ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። በደ​ላ​ቸ​ውን እም​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አላ​ስ​ብ​ምና።”


አሮ​ንም ሙሴን፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ስን​ፍና አድ​ር​ገ​ና​ልና፥ በድ​ለ​ን​ማ​ልና እባ​ክህ፥ ኀጢ​አት አታ​ድ​ር​ግ​ብን።


“ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፤” አለ። እነርሱ ግን “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፤” አሉ።


ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ብሎ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ሳያ​ስብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ር​ስ​ቶስ ዓለ​ሙን ከራሱ ጋር አስ​ታ​ር​ቆ​አ​ልና፤ የዕ​ርቅ ቃሉ​ንም በእኛ ላይ አደ​ረገ፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ው​ንም መል​እ​ክት ሰጠን።


በውኑ ስለ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመ​ር​ሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ይህን ሁሉ ትልቅ ወይም ጥቂት ቢሆን አላ​ው​ቅ​ምና ንጉሡ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር በእኔ በባ​ሪ​ያ​ውና በአ​ባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያ​ኑር” አለ።


በዚህ ክፉ ሰው በና​ባል ላይ ጌታዬ ልቡን እን​ዳ​ይ​ጥል እለ​ም​ና​ለሁ፤ እንደ ስሙ እን​ዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስን​ፍ​ናም አድ​ሮ​በ​ታል፤ እኔ ባሪ​ያህ ግን አንተ የላ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን አላ​የ​ሁም።


ሳኦ​ልም፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመ​ለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐ​ይ​ንህ ፊት ከብ​ራ​ለ​ችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላ​ደ​ር​ግ​ብ​ህም፤ እነሆ፥ ስን​ፍና እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወ​ቅሁ” አለ።


跟着我们:

广告


广告