Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዳግ​መ​ኛም የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከ​ትዬ፥ እባ​ክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮ​አ​ብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮ​ጣ​ለህ? ተመ​ለስ፤ ብት​ሄድ ይች ወሬ ለጥ​ቅም አት​ሆ​ን​ህ​ምና” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደ ገና ኢዮአብን፣ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፣ “ልጄ ሆይ፣ መሄድ ለምን አስፈለገህ? ሽልማት የሚያሰጥህ ምን የምሥራች ይዘህ ነው?” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽም እንደገና ኢዮአብን፥ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፥ “ልጄ ሆይ፥ የምሥራቹ ሽልማት እንደማያሰጥህ እያየህ መሄድ ለምን አስፈለገህ?” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ ኢዮአብን፦ የሆነ ሆኖ ኵሲን ተከትዬ፥ እባክህ፥ ልሩጥ አለው። ኢዮአብም፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም ወሬ የምትወስድ አይደለህምና ትሮጥ ዘንድ ለምን ትወድዳለህ? አለ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:22
6 交叉引用  

ኢዮ​አ​ብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየ​ኸ​ው​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢ​ዮ​አብ ሰግዶ ወጣ።


እር​ሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገ​ድ​ዳል?” አለ። እር​ሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪ​ማ​ሖ​ስም በሰ​ርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲ​ንም ቀደ​መው።


ንጉ​ሡም፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለ። አኪ​ማ​ሖ​ስም፥ “ኢዮ​አብ እኔን ባሪ​ያ​ህ​ንና የን​ጉ​ሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ብዙ ሰዎ​ችን አይ​ቻ​ለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ፈር​ዖ​ንም፥ “እነሆ፥ ከእኔ ዘንድ ወደ ሀገ​ርህ መሄድ የፈ​ለ​ግህ ምን አጥ​ተህ ነው?” አለው። አዴ​ርም፥ “አን​ዳች አላ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን ልሂድ” ብሎ መለሰ። አዴ​ርም ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።


የሚ​ያ​ሳ​ፍር ነገ​ርም፥ የስ​ን​ፍና ነገ​ርም፥ ወይም የማ​ይ​ገባ የዋዛ ነገር በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ሁን፤ ማመ​ስ​ገን ይሁን እንጂ።


跟着我们:

广告


广告