Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ኢዮ​አ​ብም፥ “አንተ በዚች ቀን የም​ሥ​ራች የም​ት​ና​ገር ሰው አይ​ደ​ለ​ህም፤ ወሬ​ውን በሌላ ቀን ትና​ገ​ራ​ለህ፤ በዚች ቀን ግን የን​ጉሡ ልጅ እንደ ሞተ ወሬ አት​ና​ገ​ርም” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኢዮአብም፣ “ዛሬ የምሥራቹን ወሬ የምትወስድለት አንተ አይደለህም፤ የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ፣ ዛሬ ሳይሆን፣ የምሥራቹን ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኢዮአብም፥ “ዛሬ የምሥራቹን ወሬ የምትወስድለት አንተ አይደለህም፤ የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ፥ ዛሬ ሳይሆን የምሥራቹን ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኢዮአብም “አይሆንም፤ ዛሬ አንተ ይዘኸው የምትሄድ ምንም ዐይነት መልካም ወሬ የለም፤ ምናልባት ሌላ ቀን ይህን ልታደርግ ትችላለህ፤ ዛሬ ግን የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ ይህን ባታደርግ ይሻላል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኢዮአብም፦ በሌላ ቀን እንጂ ዛሬ ወሬ አትናገርም፥ የንጉሥ ልጅ ሞቶአልና ዛሬ ወሬ አትናገርም አለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:20
8 交叉引用  

የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶቹ እጅ እንደ ፈረ​ደ​ለት ፈጥኜ ሄጄ ለን​ጉሥ የም​ሥ​ራች ልን​ገ​ርን?” አለ።


ኢዮ​አ​ብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየ​ኸ​ው​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢ​ዮ​አብ ሰግዶ ወጣ።


ዘበ​ኛ​ውም፥ “የፊ​ተ​ኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪ​ማ​ሖስ ሩጫ ይመ​ስ​ላል” አለ፤ “ንጉ​ሡም፦ እርሱ መል​ካም ሰው ነው፤ መል​ካ​ምም ወሬ ያመ​ጣል” አለ።


ንጉ​ሡም፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለ። አኪ​ማ​ሖ​ስም፥ “ኢዮ​አብ እኔን ባሪ​ያ​ህ​ንና የን​ጉ​ሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ብዙ ሰዎ​ችን አይ​ቻ​ለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ንጉ​ሡም እጅግ ደነ​ገጠ፤ በበ​ሩም ላይ ወዳ​ለ​ችው ሰገ​ነት ወጥቶ አለ​ቀሰ፤ ሲሄ​ድም፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ በአ​ንተ ፋንታ እኔ እን​ድ​ሞት ቤዛ​ህም እን​ድ​ሆን ማን ባደ​ረ​ገኝ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።


ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ብ​ንና አቢ​ሳን ኤቲ​ንም፥ “ለብ​ላ​ቴ​ናው ለአ​ቤ​ሴ​ሎም ስለ እኔ ራሩ​ለት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። ንጉ​ሡም ስለ አቤ​ሴ​ሎም አለ​ቆ​ቹን ሁሉ ሲያ​ዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ።


ለኢ​ዮ​አብ፥ “ንጉሡ ስለ አቤ​ሴ​ሎም ያዝ​ናል፤ ያለ​ቅ​ሳ​ልም” ብለው ነገ​ሩት።


跟着我们:

广告


广告