Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 15:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ንጉ​ሡም ሳዶ​ቅን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ከተማ መልስ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ፥ መልሶ እር​ሷ​ንና ክብ​ሯን ያሳ​የ​ኛል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከዚያም ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ከተማዪቱ ይዘህ ተመለስ፤ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ እርሱ እኔንም መልሶ ታቦቱንና ማደሪያውን እንደ ገና ለማየት ያበቃኛል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከዚያም ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ከተማይቱ ይዘህ ተመለስ፤ በጌታ ፊት ሞገስ ያገኝሁ እንደሆነ፥ እርሱ እኔንም መልሶ ታቦቱንና ማደሪያውን ያሳየኛል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከዚህ በኋላ ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ከተማይቱ መልሰህ ውሰድ፤ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኘሁ እንደ ሆነ አንድ ቀን ታቦቱንና ማደሪያውን እንዳይ ይፈቅድልኝ ይሆናል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ንጉሡም ሳዶቅን፦ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ከተማ መልስ፥ በእግዚአብሔር ዓይን ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆንሁ፥ መልሶ እርሱንና ማደሪያውን ያሳየኛል፥

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 15:25
19 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አም​ጥ​ተው ዳዊት በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ በስ​ፍ​ራዋ አኖ​ሩ​አት፤ ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሳ​ረገ።


ንጉሡ ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እኔ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጬ​አ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ግን በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።


በሰ​ማይ የም​ት​ኖር ሆይ፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ንን ወደ አንተ አነ​ሣን።


ልቤ አን​ተን አለ፦ ፊት​ህን ፈለ​ግሁ፥ አቤቱ፥ ፊት​ህን እሻ​ለሁ።


ይቅ​ር​ታና ቅን​ነት ተገ​ናኙ፤ ጽድ​ቅና ሰላም ተስ​ማሙ።


በቸ​ር​ነ​ትህ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸ​ውን ሕዝ​ብ​ህን መራህ፤ በኀ​ይ​ልህ ወደ ቅዱስ ማደ​ሪ​ያህ ጠራ​ሃ​ቸው።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለ​ኛ​ለህ፤ ነገር ግን ከእኔ ጋር የም​ት​ል​ከ​ውን አላ​ስ​ታ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም። አን​ተም ከሁሉ ይልቅ ዐወ​ቅ​ሁህ፥ ደግ​ሞም በእኔ ፊት ሞገ​ስን አገ​ኘህ አል​ኸኝ።


አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ዐው​ቅህ ዘንድ በፊ​ት​ህም ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ይህም ትልቅ ሕዝብ ሕዝ​ብህ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ ተገ​ለ​ጥ​ልኝ” አለው።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምል​ክቱ ምን​ድን ነው?” ብሎ ነበር።


“ስለ​ዚ​ህም ይህን ቃል ሁሉ ትን​ቢት ትና​ገ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ ሆኖ እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ በቅ​ዱስ ማደ​ሪ​ያ​ውም ሆኖ ድም​ፁን ያሰ​ማል፤ በበ​ረቱ ላይ እጅግ ያገ​ሣል፤ ወይ​ንም እን​ደ​ሚ​ጠ​ምቁ በም​ድር በሚ​ኖሩ ሁሉ ላይ ይጮ​ኻል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ይህ ነው እያ​ላ​ችሁ በሐ​ሰት ቃል በራ​ሳ​ችሁ አት​ታ​መኑ።


跟着我们:

广告


广告