Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 14:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አቤ​ሴ​ሎ​ምም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “በእ​ር​ሻዬ አጠ​ገብ ያለ​ች​ውን የኢ​ዮ​አ​ብን እርሻ እዩ፤ በዚ​ያም ገብስ አለው፤ ሄዳ​ችሁ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉት” አላ​ቸው። የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ብላ​ቴ​ኖች እር​ሻ​ውን አቃ​ጠ​ሉት። የኢ​ዮ​አ​ብም አሽ​ከ​ሮች ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ተመ​ል​ሰው፥ “የአ​ቤ​ሴ​ሎም አሽ​ከ​ሮች እር​ሻ​ህን በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉት” ብለው ነገ​ሩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ የኢዮአብ ዕርሻ የሚገኘው ከእኔ ዕርሻ አጠገብ ነው፤ በዕርሻው ላይ የገብስ አዝመራ አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው የኢዮአብን ዕርሻ በእሳት አቃጠሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ፥ የኢዮአብ እርሻ የሚገኘው ከእኔ እርሻ አጠገብ ነው፤ በእርሻው ላይ የገብስ ሰብል አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው እርሻውን በእሳት አቃጠሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ስለዚህም አቤሴሎም አገልጋዮቹን “ተመልከቱ፤ የኢዮአብ እርሻ ከእኔ እርሻ ቀጥሎ ሲሆን የገብስ ሰብል ይገኝበታል፤ ስለዚህም ሂዱና በእሳት አቃጥሉት” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሄደው ሰብሉን በእሳት አቃጠሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ባሪያዎቹንም፦ በእርሻዬ አጠገብ ያለውን የኢዮአብን እርሻ እዩ፥ በዚያም ገብስ አለው፥ ሂዳችሁ በእሳት አቃጥሉት አላቸው። የአቤሴሎምም ባሪያዎች እርሻውን አቃጠሉት።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 14:30
9 交叉引用  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም ወደ ንጉሡ ይል​ከው ዘንድ ወደ ኢዮ​አብ ላከ፤ ወደ እር​ሱም ሊመጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ሁለ​ተ​ኛም ላከ​በት፤ ሊመጣ ግን አል​ወ​ደ​ደም።


ኢዮ​አ​ብም ተነ​ሥቶ ወደ አቤ​ሴ​ሎም ወደ ቤቱ መጣና፥ “ብላ​ቴ​ኖ​ችህ እር​ሻ​ዬን ስለ​ምን አቃ​ጠ​ሉት?” አለው።


ኢዮ​አ​ብም፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር እን​ዲህ እዘ​ገይ ዘንድ አል​ች​ልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ገና በዛፍ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከ​ላ​ቸው።


እር​ሱም፥ “ወደ ታች ወር​ው​ሩ​አት” አላ​ቸው፤ ወረ​ወ​ሩ​አ​ትም፥ ደም​ዋም በግ​ን​ቡና በፈ​ረ​ሶች መግ​ሪያ ላይ ተረጨ፥ ረገ​ጡ​አ​ትም።


ሶም​ሶ​ንም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ክፉ ባደ​ርግ እኔ ንጹሕ ነኝ” አላ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告