Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 13:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አቤ​ሴ​ሎ​ምም አም​ኖ​ንን ክፉም ሆነ መል​ካም አል​ተ​ና​ገ​ረ​ውም። እኅ​ቱን ትዕ​ማ​ርን ስላ​ስ​ነ​ወ​ራት አቤ​ሴ​ሎም አም​ኖ​ንን ጠል​ቶ​ታ​ልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ ደግ አንዳች ቃል አልተናገረውም፤ ምክንያቱም አምኖን እኅቱን ትዕማርን ስላስነወራት ጠልቶት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አቤሴሎም ግን አምኖን እኅቱን ትዕማርን ስለደፈራት፥ ከጥላቻው የተነሣ አምኖንን ክፉም ሆነ ደግ አንዳች ቃል አልተናገረውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የእኅቱን የትዕማርን ክብረ ንጽሕና በመድፈሩም ምክንያት አቤሴሎም አምኖንን እጅግ ጠላው፤ ዳግመኛም ክፉም ሆነ ደግ ሊያነጋግረው አልፈለገም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አቤሴሎምም እኅቱን ትዕማርን ስላሳፈራት አምኖንን ጠልቶታልና አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካምም አልተናገረውም።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 13:22
19 交叉引用  

ባቱ​ኤ​ልና ላባም መለሱ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መጥ​ቶ​አል፤ ክፉ ወይም በጎ ልን​መ​ል​ስ​ልህ አን​ች​ልም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሶር​ያ​ዊው ወደ ላባ በሌ​ሊት በሕ​ልም መጥቶ፥ “በባ​ሪ​ያዬ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ክፉ ነገር እን​ዳ​ት​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።


አሁ​ንም በአ​ንተ ላይ ክፉ ማድ​ረግ በቻ​ልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ትና​ንት፦ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ተጠ​ን​ቀቅ ብሎ ነገ​ረኝ።


ንጉ​ሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ ሰማ፤ እጅ​ግም ተቈጣ፥ ነገር ግን የበ​ኵር ልጁ ነበ​ረና ስለ ወደ​ደው የል​ጁን የአ​ም​ኖ​ንን ነፍስ አላ​ሳ​ዘ​ነም።


ልዝብ ከንፈሮች ጥልን ይሸፍናሉ፤ ስድብን የሚያወጡ ግን ሰነፎች ናቸው።


በመ​ን​ፈ​ስህ ለቍጣ ችኩል አት​ሁን፥ ቍጣ በሰ​ነ​ፎች ብብት ያር​ፋ​ልና።


“ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤


ተቈጡ፤ አት​በ​ድ​ሉም፤ ፀሐይ ሳይ​ጠ​ል​ቅም ቍጣ​ች​ሁን አብ​ርዱ።


መራ​ራ​ነ​ት​ንና ቍጣን፥ ብስ​ጭ​ት​ንና ርግ​ማ​ንን፥ ጥፋ​ት​ንና ስድ​ብን ሁሉ ከክፉ ነገር ሁሉ ጋር ከእ​ና​ንተ አርቁ።


ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።


በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።


ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።


ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።


跟着我们:

广告


广告