2 ሳሙኤል 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ትዕማርም አመድ ወስዳ በራስዋ ላይ ነሰነሰች፤ በላይዋ የነበረውንም ብዙ ኅብር ያለውን ልብስዋን ቀደደችው፤ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ትዕማርም በራሷ ላይ ዐመድ ነሰነሰች፤ ጌጠኛ ልብሷን ቀደደች፤ ከዚያም እጇን በራሷ ላይ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ትዕማርም በራሷ ላይ ዐመድ ነስንሳ፤ ለብሳው የነበረውን መጐናጸፊያ ቀዳደደች፤ እጇንም በራሷ ላይ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች። 参见章节 |