Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለድ​ሃው ግን ከገ​ዛት አን​ዲት ታናሽ በግ በቀር አን​ዳች አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ አሳ​ደ​ጋ​ትም፤ ተን​ከ​ባ​ከ​ባ​ትም፤ ከእ​ር​ሱና ከል​ጆቹ ጋር አደ​ገች፤ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ትበላ፥ ከዋ​ን​ጫ​ውም ትጠጣ፥ በብ​ብ​ቱም ትተኛ ነበረ፤ እንደ ልጁም ነበ​ረች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ድኻው ግን ከገዛት ከአንዲት ጠቦት በግ በቀር ሌላ አልነበረውም። ተንከባከባት፤ ዐብራውም ከልጆቹ ጋራ አደገች፤ ዐብራው ትበላ፤ ከጽዋው ትጠጣ እንዲሁም በዕቅፉ ትተኛ ነበር፤ ልክ እንደ ገዛ ልጁ ነበረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ድኻው ግን ከገዛት ከአንዲት ጠቦት በግ በስተቀር ሌላ አልነበረውም። እየተንከባከበ አብራውም ከልጆቹ ጋር አደገች፤ አብራው ትበላ፤ ከጽዋውም ትጠጣ እንዲሁም በዕቅፉ ትተኛ ነበር፤ ልክ እንደገዛ ልጁ ነበረች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ድኻው ግን በገንዘቡ የገዛት አንዲት የበግ ግልገል ብቻ ነበረችው፤ እርስዋን እየተንከባከበ ከልጆቹ ጋር በቤቱ ውስጥ ያሳድጋት ነበር፤ ከሚመገበው ይመግባት፥ ከሚጠጣውም ያጠጣት ነበር፤ ስትተኛም ያቅፋት ነበር፤ ያቺም ግልገል ልክ እንደ ልጁ ነበረች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ለድሀው ግን ከገዛት አንዲት ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውም፥ አሳደጋትም፥ ከልጆቹም ጋር በእርሱ ዘንድ አደገች፥ እንጀራውንም ትበላ፥ ከዋንጫውም ትጠጣ፥ በብብቱም ትተኛ ነበር፥ እንደ ልጁም ነበረች።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 12:3
6 交叉引用  

ዳዊ​ትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤ​ል​ያብ ልጅ የኬ​ጤ​ያ​ዊው የኦ​ርዮ ሚስት ቤር​ሳ​ቤህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?” አለው።


ባለ​ጠ​ጋ​ውም እጅግ ብዙ የበ​ግና የላም መንጋ ነበ​ረው።


ወደ ባለ​ጠ​ጋ​ውም እን​ግዳ በመጣ ጊዜ ከበ​ጉና ከላሙ ወስዶ ለዚያ ወደ እርሱ ለመ​ጣው እን​ግዳ ያዘ​ጋ​ጅ​ለት ዘንድ ሳሳ፤ የዚ​ያ​ንም የድ​ሃ​ውን ሰው በግ ወስዶ ለዚያ ለመ​ጣው ሰው አዘ​ጋጀ።


ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።


“የአ​ባ​ትህ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥


跟着我们:

广告


广告