Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 1:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እና​ንተ የጌ​ላ​ቡሄ ተራ​ሮች ሆይ፥ ዝና​ብና ጠል አይ​ው​ረ​ድ​ባ​ችሁ፤ ቍር​ባ​ን​ንም የሚ​ያ​በ​ቅል እርሻ አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ። የኀ​ያ​ላን ጋሻ በዚያ ወድ​ቆ​አ​ልና፤ የሳ​ኦ​ልም ጋሻ ዘይት አል​ተ​ቀ​ባ​ምና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ ጠል አያረስርሳችሁ፤ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቍርባን እህል የሚያበቅሉም ዕርሻዎች አይኑራቸው፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሷልና፤ የሳኦል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፥ የሳኦል ጋሻ በዘይት እንዳልተቀባ፥ የኃያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፥ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 1:21
14 交叉引用  

በዚ​ያም ወራት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፥ ተወ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።


በነ​ጋ​ውም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦ​ል​ንና ልጆ​ቹን በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኙ​አ​ቸው።


አን​ገ​ትሽ ለሰ​ልፍ ዕቃ መስ​ቀያ እንደ ተሠራ እንደ ዳዊት ግንብ ነው፤ በው​ስ​ጡም ሺህ የጦር ዕቃና የኀ​ያ​ላን መሣ​ሪያ ሁሉ ተሰ​ቅ​ሎ​በ​ታል።


ማዕ​ዱን አዘ​ጋጁ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እና​ንተ አለ​ቆች ሆይ፥ ተነሡ፤ ጋሻ​ው​ንም አዘ​ጋጁ።


ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወ​ረ​ደ​በት ቀን ልቅ​ሶን አስ​ለ​ቀ​ስሁ፤ ቀላ​ዩ​ንም ስለ እርሱ ሸፈ​ን​ሁት፤ ፈሳ​ሾ​ች​ንም ከለ​ከ​ልሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም ውኆች ተከ​ለ​ከሉ፤ ሊባ​ኖ​ስ​ንም ስለ እርሱ አሳ​ዘ​ን​ሁት። የዱ​ርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።


መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተወ​ግ​ዶ​አል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሠ​ውያ የም​ታ​ገ​ለ​ግሉ ካህ​ናቱ፥ አል​ቅሱ።


የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ አለ፥ “ሜሮ​ዝን ርገሙ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በኀ​ያ​ላን መካ​ከል ወደ እርሱ ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በቤ​ቶ​ችዋ ያሉ​ትን ሰዎች ፈጽ​ማ​ችሁ ርገሙ።”


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦ​ልና ሦስቱ ልጆቹ በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኙ​አ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告