Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በሰ​ሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥ​ነው ልብ​ሳ​ቸ​ውን ወሰዱ፤ በሰ​ገ​ነቱ መውጫ እር​ከን ላይም ከእ​ግሩ በታች አነ​ጠ​ፉት፥ መለ​ከ​ትም እየ​ነፉ፥ “ኢዩ ነግ​ሦ​አል” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያ ሁሉም ቶሎ ብለው ልብሳቸውን እያወለቁ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ ከዚያም መለከት ነፍተው፣ “ኢዩ ነግሧል” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሁሉም ፈጥነው ልባሳቸውን ወሰዱ፤ በሰገነቱ መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት፤ ቀንደ መለከትም እየነፉ፥ “ኢዩ ነግሦአል!” አሉ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 9:13
12 交叉引用  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “የመ​ለ​ከት ድምፅ በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ አቤ​ሴ​ሎም በኬ​ብ​ሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበ​ኞ​ችን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ላከ።


እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን ጠር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በፊቱ እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፦ አዶ​ን​ያስ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ ይላሉ።


በዚ​ያም ካህኑ ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቀብ​ተው ያን​ግ​ሡት፤ መለ​ከ​ትም ነፍ​ታ​ችሁ፦ ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ በሉ።


ካህ​ኑም ሳዶቅ ከድ​ን​ኳኑ የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎ​ሞ​ንን ቀባ፤ መለ​ከ​ትም ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” አሉ።


የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ ቀብ​ቶም አነ​ገ​ሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” እያሉ በእ​ጃ​ቸው አጨ​በ​ጨቡ።


እነ​ሆም፥ ንጉ​ሡን እንደ ተለ​መ​ደው በዓ​ምዱ አጠ​ገብ ቆሞ፥ ከን​ጉ​ሡም ጋር መዘ​ም​ራ​ንና መለ​ከ​ተ​ኞች ቆመው አየች፤ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎ​አ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር። ጎቶ​ል​ያም ልብ​ስ​ዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች።


እነ​ር​ሱም፥ “ዋሸ​ኸን፤ ነገር ግን ንገ​ረን” አሉት፤ ኢዩም፦ ለጌ​ታው ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ ብሎ እን​ዲ​ህና እን​ዲህ ነገ​ረኝ” አላ​ቸው።


ሙሴና አሮን በክ​ህ​ነ​ታ​ቸው ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና ሳሙ​ኤ​ልም ስሙን ከሚ​ጠ​ሩት ጋራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠሩት፥ እር​ሱም መለ​ሰ​ላ​ቸው።


ሲሄ​ዱም በመ​ን​ገድ ልብ​ሳ​ቸ​ውን አነ​ጠፉ።


跟着我们:

广告


广告