Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ንጉ​ሡም አዛ​ሄ​ልን፥ “ገጸ በረ​ከት በእ​ጅህ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው ተቀ​በ​ለው፤ ከዚ​ህም በሽታ እድን እንደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠይ​ቀው” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ንጉሡም አዛሄልን፣ “ገጸ በረከት ይዘህ ሂድና የእግዚአብሔርን ሰው ተገናኘው። በርሱም አማካይነት፣ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ብለህ እግዚአብሔርን ጠይቅ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለ ሥልጣኖች አንዱ የሆነውን አዛሄልን ጠርቶ፥ “ለነቢዩ ስጦታ ይዘህ ሂድና እኔ ከዚህ በሽታ እድን ወይም አልድን እንደሆነ እግዚአብሔርን እንዲጠይቅልኝ ለምነው” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነውን አዛሄልን ጠርቶ፥ “ለነቢዩ ስጦታ ይዘህ ሂድና እኔ ከዚህ በሽታ እድን ወይም አልድን እንደ ሆነ እግዚአብሔርን እንዲጠይቅልኝ ለምነው” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ንጉሡም አዛሄልን “ገጸ በረከት በእጅህ ወስደህ የእግዚአብሔርን ሰው ልትገናኝ ሂድ፤ በእርሱም አፍ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ብለህ እግዚአብሔርን ጠይቅ፤” አለው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 8:8
11 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ሂድ፤ በመ​ጣ​ህ​በ​ትም መን​ገድ በም​ድረ በዳ ወደ ደማ​ስቆ ተመ​ለስ፤ ከዚ​ያም በደ​ረ​ስህ ጊዜ በሶ​ርያ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ አዛ​ሄ​ልን ቅባው፤


ከአ​ዛ​ሄ​ልም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኢዩ ይገ​ድ​ለ​ዋል፤ ከኢ​ዩም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኤል​ሳዕ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ለምን ላክህ? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም” አለው።


አካ​ዝ​ያ​ስም በሰ​ማ​ርያ በሰ​ገ​ነቱ ላይ ሳለ በዐ​ይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ጠይቁ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊጠ​ይ​ቁ​ለት ሄዱ።


እነ​ር​ሱም፥ “አንድ ሰው ሊገ​ና​ኘን መጣና፦ ሂዱ፤ ወደ ላካ​ችሁ ንጉሥ ተመ​ል​ሳ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ የላ​ክህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ስለ​ዚህ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በሉት አለን” አሉት።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ንዕ​ማ​ንን፥ “ሂድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ደብ​ዳቤ እል​ካ​ለሁ” አለው። እር​ሱም ሄደ፤ ዐሥ​ርም መክ​ሊት ብር፥ ስድ​ስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥ​ርም መለ​ወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።


አንድ ሰውም፥ “አቤቱ የሚ​ድኑ ጥቂ​ቶች ናቸ​ውን?” አለው። እርሱ ግን እን​ዲህ አላ​ቸው፦


ወደ ውጭም አው​ጥቶ “ጌቶች፥ እድን ዘንድ ምን ላድ​ርግ?” አላ​ቸው።


ሳኦ​ልም አብ​ሮት ያለ​ውን ብላ​ቴና፥ “እነሆ! እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ምን እን​ወ​ስ​ድ​ለ​ታ​ለን? እን​ጀራ ከከ​ረ​ጢ​ታ​ችን አል​ቆ​አ​ልና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የም​ን​ወ​ስ​ድ​ለት ምንም የለ​ንም” አለው።


跟着我们:

广告


广告