2 ነገሥት 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ወደ ሰማርያም በገቡ ጊዜ ኤልሳዕ፥ “አቤቱ፥ ያዩ ዘንድ የእነዚህን ሰዎች ዐይኖች ግለጥ” አለ፤ እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን ገለጠ፤ እነርሱም አዩ። እነሆም፥ በሰማርያ መካከል እንዳሉ ዐወቁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ወደ ከተማዪቱም ከገቡ በኋላ ኤልሳዕ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲያዩ የእነዚህን ሰዎች ዐይን ክፈት” አለ። እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን ከፈተ። እነርሱም በሰማርያ ውስጥ መሆናቸውን አዩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ወደ ከተማይቱም እንደ ገቡ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችሉ ዐይኖቻቸውን ግለጥላቸው!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን በከፈተላቸው ጊዜ በሰማርያ ውስጥ መሆናቸውን ተረዱ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ወደ ከተማይቱም እንደ ገቡ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችሉ ዐይኖቻቸውን ግለጥላቸው!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን በከፈተላቸው ጊዜ በሰማርያ ውስጥ መሆናቸውን ተረዱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ወደ ሰማርያም በገቡ ጊዜ ኤልሳዕ “አቤቱ! ያዩ ዘንድ የእነዚህን ሰዎች ዐይኖች ግለጥ፤” አለ፤ እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን ገለጠ፤ እነርሱም አዩ። እነሆም፥ በሰማርያ መካከል ነበሩ። 参见章节 |