Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 5:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እር​ሱም፥ “ያ ሰው ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ ሊቀ​በ​ልህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ልቤ ከአ​ንተ ጋር አል​ሄ​ደ​ምን? አሁ​ንም ወር​ቁ​ንና ልብ​ሱን፥ ተቀ​ብ​ለ​ሃል፤ ለወ​ይን ቦታ፥ ለመ​ሰ​ማ​ርያ ቦታና ለዘ​ይት ቦታ፥ ለላ​ሞ​ችና ለበ​ጎች፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ባሮች ይሁ​ንህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ኤልሳዕ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው ሊገናኝህ ከሠረገላው ሲወርድ፣ መንፈሴ ከአንተ ጋራ አልሄደምን? እንዲያው ለመሆኑ ጊዜው ገንዘብና ልብስ፣ የወይራ ዘይት ተክልና የወይን ተክል ቦታ፣ የበግና የከብት መንጋ፣ ወንድና ሴት አገልጋይ የሚቀበሉበት ነውን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ኤልሳዕም “ሰውየው ሊያነጋግርህ ከሠረገላው ላይ ሲወርድ እኔ በመንፈስ ከአንተ ጋር አልነበርኩምን? እነሆ አሁን ገንዘብና ልብስ፥ የወይራና የወይን ተክል ቦታ፥ በግና የቀንድ ከብት ወይም አገልጋዮችን ለመቀበል ጊዜው አይደለም!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ኤልሳዕም “ሰውየው ሊያነጋግርህ ከሠረገላው ላይ ሲወርድ እኔ በመንፈስ ከአንተ ጋር አልነበርኩምን? እነሆ አሁን ገንዘብና ልብስ፥ የወይራና የወይን ተክል ቦታ፥ በግና የቀንድ ከብት ወይም አገልጋዮችን ለመቀበል ጊዜው አይደለም!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እርሱም “ያ ሰው ከሠረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? ብሩንና ልብሱን፥ የወይራውንና የወይኑን ቦታ፥ በጎችንና በሬዎችን፥ ወንዶችንና ሴቶችን ባሪያዎች ትቀበል ዘንድ ይህ ጊዜው ነውን?

参见章节 复制




2 ነገሥት 5:26
18 交叉引用  

አንተ፦ አብ​ራ​ምን ባለ​ጠጋ አደ​ረ​ግ​ሁት እን​ዳ​ትል፥ ከአ​ንተ ገን​ዘብ ሁሉ ፈት​ልም ቢሆን፥ የጫማ ማዘ​ቢ​ያም ቢሆን እን​ዳ​ል​ወ​ስድ፥


ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አል​ቀ​በ​ልም” አለ። ይቀ​በ​ለ​ውም ዘንድ ግድ አለው፤ እርሱ ግን እንቢ አለ።


ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ነቢዩ ኤል​ሳዕ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በእ​ል​ፍ​ኝህ ውስጥ ሆነህ የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና ቃል​ህን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እርሱ ይነ​ግ​ረ​ዋል፤” አለ።


የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።


ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።


ለራ​ስህ ታላ​ላቅ ነገ​ሮ​ችን ትፈ​ል​ጋ​ለ​ህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ እነሆ ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለ​ሁና አት​ፈ​ል​ጋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በሄ​ድ​ህ​በት ስፍራ ሁሉ ነፍ​ስ​ህን እንደ ምርኮ አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?


ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፤ በከንቱ ስጡ።


ወር​ቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብ​ስም ቢሆን ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ ስንኳ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም።


በድ​ካ​ማ​ች​ንና በሥ​ራ​ችን ነዳ​ያ​ንን እን​ቀ​በ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ደ​ሚ​ገ​ባን ይህን አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ‘ከሚ​ቀ​በል ይልቅ የሚ​ሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለ​ው​ንም የጌ​ታ​ች​ንን የኢ​የ​ሱ​ስን ቃል ዐስቡ።”


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ትፈ​ታ​ተ​ኑት ዘንድ እን​ዴት ተባ​በ​ራ​ችሁ? እነሆ፥ ባል​ሽን የቀ​በ​ሩት ሰዎች እግ​ሮች በበር ናቸው፤ አን​ቺ​ንም ይወ​ስ​ዱ​ሻል” አላት።


እኔ በሥ​ጋዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ባል​ኖር፥ በመ​ን​ፈሴ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠ​ራ​ውን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ።


እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል።


跟着我们:

广告


广告