Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 3:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እንደ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውና ድል እን​ደ​ነ​ሡ​አ​ቸው ባየ ጊዜ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰባት መቶ ሰዎ​ችን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ወደ ኤዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ያልፉ ዘንድ ሞከሩ፤ አል​ቻ​ሉ​ምም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የሞዓባውያን ንጉሥ በጦርነቱ መሸነፉን እንዳወቀ፣ ሰይፍ የታጠቁ ሰባት መቶ ሰዎች ይዞ የኤዶም ንጉሥ ወዳለበት ጥሶ ለመግባት ሞከረ፤ ነገር ግን አልተሳካላቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የሞዓብ ንጉሥ ድል እንደ ተመታ ባረጋገጠ ጊዜ ሰይፍ የታጠቁ ሰባት መቶ ሰዎችን አስከትሎ የጠላት ጦር የተሰለፈበትን መስመር ጥሶ ለማምለጥና ወደ ሶርያ ንጉሥ ለመሄድ ቢሞክርም ከቶ አልተሳካለትም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የሞአብ ንጉሥ ድል እንደ ተመታ ባረጋገጠ ጊዜ ሰይፍ የታጠቁ ሰባት መቶ ሰዎችን አስከትሎ የጠላት ጦር የተሰለፈበትን መስመር ጥሶ ለማምለጥና ወደ ሶርያ ንጉሥ ለመሄድ ቢሞክርም ከቶ አልተሳካለትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የሞዓብም ንጉሥ ሰልፍ እንደ በረታበት ባየ ጊዜ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰባት መቶ ሰዎች ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ወደ ኤዶምያስም ንጉሥ ያልፉ ዘንድ ሞከሩ፤ አልቻሉምም።

参见章节 复制




2 ነገሥት 3:26
5 交叉引用  

ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሱ፤ በመ​ል​ካ​ሞ​ቹም እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ እስ​ኪ​ሞሉ ድረስ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው አንድ አንድ ድን​ጋይ ይጥል ነበር፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወን​ጭ​ፎ​ችም ከብ​በው መቱ​አ​ቸው።


ከዚህ በኋላ በእ​ርሱ ፋንታ ንጉሥ የሚ​ሆ​ነ​ውን የበ​ኵር ልጁን ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቅ​ጥሩ ላይ አቀ​ረ​በው። እስ​ራ​ኤ​ልም ታላቅ ጸጸት ተጸ​ጸቱ፤ ከዚ​ያም ርቀው ወደ ምድ​ራ​ቸው ተመ​ለሱ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ሄዱ፤ የሰ​ባ​ትም ቀን መን​ገድ ዞሩ፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱና ለሚ​ጫኑ እን​ስ​ሶች ውኃ አጡ።


በእ​ር​ሱም ዘመን የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች ሸፍ​ተው የይ​ሁዳ ሰዎ​ችን ከዱ​አ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ንጉሥ አነ​ገሡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ንጉሥ አጥ​ንት አመድ እስ​ኪ​ሆን ድረስ አቃ​ጥ​ሎ​ታ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የሞ​ዓብ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


跟着我们:

广告


广告