Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የሎ​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። የእናቱም ስም አሚጣል ነበረ፤ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ አንድ ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የነበረው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አንድ ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የነበረው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም አሚጣል የተባለች የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።

参见章节 复制




2 ነገሥት 24:18
8 交叉引用  

ዮአ​ክ​ስም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ነገሠ። እና​ቱም አሚ​ጣል ትባል ነበር፥ እር​ስ​ዋም የሎ​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ መጣ።


ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ፥ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ የገ​ባ​ዖን ሰው የዓ​ዙር ልጅ ሐና​ንያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በካ​ህ​ና​ትና በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በይ​ሁዳ ያነ​ገ​ሠው የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ በኢ​ኮ​ን​ያን ፋንታ ነገሠ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።


跟着我们:

广告


广告