Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 24:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብት ከዚያ አወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ የሠ​ራ​ውን የወ​ር​ቁን ዕቃ ሁሉ ሰባ​በረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የቤተ መንግሥቱን ሀብት በሙሉ አጋዘ፤ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያሠራቸውንም የወርቅ ዕቃዎች ሁሉ ወሰደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ ጠራርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደ። ቀደም ሲል እግዚአብሔር በተናገረውም ቃል መሠረት ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አሠርቶት የነበረውን የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰባበረው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ ጠራርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደ። ቀደም ሲል እግዚአብሔር በተናገረውም ቃል መሠረት ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አሠርቶት የነበረውን የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰባበረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእግዚአብሔርንም ቤት ቤተ መዛግብት ሁሉ የንጉሡንም ቤተ መዛግብት ከዚያ አወጣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሠራውን የወርቁን ዕቃ ሁሉ ሰባበረ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 24:13
15 交叉引用  

እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አይ​ቀ​ርም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ አያ​ሌ​ውን አው​ጥቶ ወደ ባቢ​ሎን ወሰደ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም በጣ​ዖቱ ቤት ውስጥ አኖ​ረው።


እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አያ​ስ​ቀ​ሩ​ል​ህም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በሜዳ ያለው ተራ​ራዬ ሆይ! ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ሁሉ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ህ​ንም ስለ ኀጢ​አ​ትህ በድ​ን​በ​ሮ​ችህ ሁሉ ለመ​በ​ዝ​በዝ እሰ​ጣ​ለሁ።


የዚ​ች​ንም ከተማ ኀይል ሁሉ፥ ጥሪ​ቷ​ንም ሁሉ፥ ክብ​ር​ዋ​ንም ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ነገ​ሥ​ታት መዝ​ገብ ሁሉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ርሱ ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ይዘ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ያስ​ገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።


ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ አለ፥ “አሜን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ፥ ምር​ኮ​ው​ንም ሁሉ ከባ​ቢ​ሎን ወደ​ዚህ ስፍራ በመ​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ትን​ቢት ይፈ​ጽም።


ልብ​ስ​ሽ​ንም ይገ​ፍ​ፉ​ሻል፤ የክ​ብ​ር​ሽ​ንም ጌጥ ይወ​ስ​ዳሉ።


በባ​ዕ​ድም እጅ ለን​ጥ​ቂያ፥ በም​ድር ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችም እጅ ለብ​ዝ​በዛ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ያረ​ክ​ሱ​አ​ቸ​ዋል።


跟着我们:

广告


广告