Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 23:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ፈር​ዖን ኒካዑ በኤ​ማት ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ አሰ​ረው፤ በም​ድ​ሩም ላይ መቶ መክ​ሊት ብርና አንድ መቶ መክ​ሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለ​በት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በኢየሩሳሌም ተቀምጦ እንዳይገዛም ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ሪብላ በምትባል ቦታ አሰረው፤ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እርሱንም ኒካዑ ተብሎ የሚጠራው የግብጽ ንጉሥ ኢዮአካዝ በኢየሩሳሌም እንዳይነግሥ በሐማት ምድር በምትገኘው በሪብላ እስረኛ በማድረግ፥ ይሁዳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ብር፥ ሠላሳ አራት ኪሎ ወርቅ ግብር እንዲከፍል ባደረገው ጊዜ የኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እርሱንም ኒካዑ ተብሎ የሚጠራው የግብጽ ንጉሥ ኢዮአካዝ በኢየሩሳሌም እንዳይነግሥ በሐማት ምድር በምትገኘው በሪብላ እስረኛ በማድረግ፥ ይሁዳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ብር፥ ሠላሳ አራት ኪሎ ወርቅ ግብር እንዲከፍል ባደረገው ጊዜ የኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ባለችው በሪብላ አሰረው፤ በምድሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለበት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 23:33
18 交叉引用  

በዚ​ያም ዘመን ሰሎ​ሞን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠ​ራው ቤት ውስጥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፥ ደስ​ታም እያ​ደ​ረጉ ሰባት ቀን በዓ​ሉን አከ​በሩ።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ “በድ​ያ​ለሁ፥ ከእኔ ተመ​ለስ፤ የም​ት​ጭ​ን​ብ​ኝ​ንም ሁሉ እሸ​ከ​ማ​ለሁ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ላይ ሦስት መቶ መክ​ሊት ብርና ሠላሳ መክ​ሊት ወርቅ ጫነ​በት።


በእ​ር​ሱም ዘመን የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ሊጋ​ጠም ወደ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉ​ሡም ኢዮ​ስ​ያስ ከእ​ርሱ ጋር ሊጋ​ጠም ወጣ፤ ፈር​ዖ​ንም በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ በመ​ጊዶ ገደ​ለው።


ኢዮ​አ​ቄ​ምም ብሩ​ንና ወር​ቁን ለፈ​ር​ዖን ሰጠው፤ እንደ ፈር​ዖ​ንም ትእ​ዛዝ ገን​ዘብ ይሰጥ ዘንድ ምድ​ሩን አስ​ገ​በረ፤ ለፈ​ር​ዖን ኒካ​ዑም ግብር ይሰጥ ዘንድ ከሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ እንደ ግም​ጋ​ሜው ብርና ወርቅ አስ​ከ​ፈለ።


የአ​በ​ዛ​ዎ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ማርኮ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት ወደ ዴብ​ላታ አመ​ጣ​ቸው።


ንጉ​ሡ​ንም ይዘው የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ዴብ​ላታ ወሰ​ዱት፤ ፍር​ድም ፈረ​ዱ​በት።


“ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ ያረ​ገ​ዘ​ች​ንም ሴት ቢያ​ቈ​ስሉ ተሥ​ዕ​ሎተ መል​ክእ ያል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ለት ፅን​ስም ቢያ​ስ​ወ​ር​ዳት፥ የሴ​ቲቱ ባል የጣ​ለ​በ​ትን ያህል ካሳ ይክ​ፈል፤


ዐሳበ ክፉ ሰው ብዙ ያጠፋል፤ ጽኑ ደፋር ቢሆን ግን ነፍሱን ይጨምራል።


በግ​ብፅ ላይ፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ በከ​ር​ኬ​ማስ በነ​በ​ረው፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ታው በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ኒካዑ ሠራ​ዊት፥


ተዘ​ል​ሎም ይኖ​ራል፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አጠፋ፤ ሀገ​ራ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሰ፤ ከግ​ሣ​ቱም ድምፅ የተ​ነሣ ምድ​ርና ሞላዋ ጠፋች።


በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው በቀፎ ውስጥ አኖ​ሩት፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አመ​ጡት፤ ድም​ፁም በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እን​ዳ​ይ​ሰማ ወደ ግዞት ቤት አገ​ቡት።


ወጡም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ማት ዳር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።


ዳር​ቻ​ውም ከሴ​ፋማ በዐ​ይን ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ወደ አር​ቤላ ይወ​ር​ዳል፤ እስከ ኬኔ​ሬት የባ​ሕር ወሽ​መጥ በም​ሥ​ራቅ በኩል ይደ​ር​ሳል፤


跟着我们:

广告


广告