Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 23:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን እን​ዳ​ራ​ቅ​ሁት ይሁ​ዳን ከፊቴ አር​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ትን ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና፦ ስሜ በዚያ ይሆ​ናል ያል​ሁ​ት​ንም ቤት እጥ​ላ​ለሁ” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “እስራኤልን እንዳስወገድሁ ሁሉ ይሁዳንም ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኋትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና፣ ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’ ብዬ የተናገርሁለትን ይህን ቤተ መቅደስ እተዋለሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእስራኤል ላይ ያደረግኹትን ነገር ሁሉ በይሁዳም ላይ አደርጋለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ሕዝብ ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኳትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራል ብዬ የነበረውንም ቤተ መቅደስ እተዋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእስራኤል ላይ ያደረግኹትን ነገር ሁሉ በይሁዳም ላይ አደርጋለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ሕዝብ ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኳትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራል ብዬ የነበረውንም ቤተ መቅደስ እተዋለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እግዚአብሔርም “እስራኤልን እንዳራቅሁት ይሁዳን ከፊቴ አርቀዋላሁ፤ ይህችንም የመረጥኋትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ‘ስሜ በዚያ ይሆናል፤’ ያልሁትን ቤት እጥላለሁ፤” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 23:27
26 交叉引用  

ባሪ​ያህ ወደ​ዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ሌሊ​ትና ቀን የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “በፊቴ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ጸሎ​ት​ህ​ንና ልመ​ና​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እንደ ጸሎ​ት​ህም ሁሉ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠ​ራ​ኸ​ውን ቤት ቀድ​ሻ​ለሁ፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም በዘ​መኑ ሁሉ በዚያ ይሆ​ናሉ።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ከፊ​ቱም ጣላ​ቸው፤ ከይ​ሁ​ዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸ​ውም፤ ከፊ​ቱም እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ በበ​ዝ​ባ​ዦች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እስ​ራ​ኤ​ልን ከፊቱ እስ​ኪ​ያ​ወጣ ድረስ ከእ​ር​ስዋ አል​ራ​ቁም። እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ ከም​ድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ አሦር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፥ በሜ​ዶ​ንም አው​ራ​ጃ​ዎች አኖ​ራ​ቸው፤


የሰ​ማ​ር​ያ​ንም ገመድ የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ቤት ቱንቢ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ የሽቱ ዕቃ እን​ዲ​ወ​ለ​ወል ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ወል​ውዬ በፊቷ እገ​ለ​ብ​ጣ​ታ​ለሁ።


የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቅሬታ እጥ​ላ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ምር​ኮና ብዝ​በዛ ይሆ​ናሉ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ስሜን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ለሁ” ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መሠ​ዊ​ያን ሠራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለዳ​ዊ​ትና ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን፥ “በዚህ ቤት ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጥ​ኋት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስሜን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አኖ​ራ​ለሁ፤


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ስ​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን አደጋ ጣዮች፥ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደ​ደ​በት፤ በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያጠ​ፉት ዘንድ በይ​ሁዳ ላይ ሰደ​ዳ​ቸው።


ምና​ሴም ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ከፊቱ ያር​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ሆነ፤


የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ መታ​ቸው፥ በኤ​ማ​ትም ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው። እን​ዲ​ሁም ይሁዳ ከሀ​ገሩ ተማ​ረከ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምናሴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ አደ​ረ​ገው ሁሉ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል ለመ​ከራ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የል​ቡን ዐሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ያው​ቁ​ታል።


ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ምን​ድር ነው?” ብሎ ቢጠ​ይ​ቅህ፥ አንተ፥ “ሸክሙ እና​ንተ ናችሁ፤ እጥ​ላ​ች​ሁ​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ስለ​ዚህ፥ እነሆ- ፈጽሜ እረ​ሳ​ች​ኋ​ለሁ እና​ን​ተ​ንም፥ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የሰ​ጠ​ኋ​ትን ከተማ ከፊቴ አን​ሥቼ እጥ​ላ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ እጅግ ከፍ ቢል፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ፈጽሞ ዝቅ ቢል በዚያ ጊዜ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ሁሉ እን​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከፊቴ አስ​ወ​ግ​ዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከሠ​ሩ​አት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በቁ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ ውስጥ ናትና፤


“ይህ ሕዝብ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ወገን ጥሎ​አ​ቸ​ዋል፥ እን​ዲሁ በፊ​ታ​ቸው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝ​ቤን አቃ​ል​ለ​ዋል ያለ​ውን ነገር አት​መ​ለ​ከ​ት​ምን?


ዛይ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያ​ውን ጣለ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ጠላው፤ የአ​ዳ​ራ​ሾ​ች​ዋ​ንም ቅጥር በጠ​ላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ድም​ፃ​ቸ​ውን በዕ​ል​ልታ አሰሙ።


跟着我们:

广告


广告