Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ደግ​ሞም በቤ​ቴል ኮረ​ብታ የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ያሳተ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ያሠ​ራ​ውን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገጃ፥ ይህ​ንም መሠ​ዊ​ያና መስ​ገጃ አፈ​ረሰ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱ​ንም አቃ​ጠ​ለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እስራኤልን ባሳተው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም የተሠራውን መሠዊያ፣ በቤቴል የነበረውን ያን የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራ፣ መሠዊያው ያለበትን ያን የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራ እንኳ እንደዚሁ አፈረሰ፤ ድንጋዮቹን ሰባበረ፤ እንደ ዱቄትም አደቀቃቸው፤ የአሼራንም ምስል ዐምድ አቃጠለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤል አሠርቶት የነበረውን የማምለኪያ ቦታ ኢዮስያስ አፈራርሶ ጣለ፤ መሠዊያውን ነቅሎ፥ የተሠራበትን ድንጋይ ሁሉ ሰባብሮ በማድቀቅ እንደ ትቢያ አደረገው፤ የአሼራንም ምስል በእሳት አቃጠለ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤል አሠርቶት የነበረውን የማምለኪያ ቦታ ኢዮስያስ አፈራርሶ ጣለ፤ መሠዊያውን ነቅሎ፥ የተሠራበትን ድንጋይ ሁሉ ሰባብሮ በማድቀቅ እንደ ትቢያ አደረገው፤ የአሼራንም ምስል በእሳት አቃጠለ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ደግሞም በቤቴል የነበረውን መሠዊያ፥ እስራኤልንም ያሳተ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያሠራውን የኮረብታውን መስገጃ፥ ይህን መሠዊያና መስገጃ አፈረሰ፤ ድንጋዮቹንም ሰባበረ፤ አድቅቆም ትቢያ አደረገው፤ የማምለኪያ ዐፀዱንም አቃጠለው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 23:15
16 交叉引用  

ንጉ​ሡም ተማ​ከረ፤ ሁለ​ትም የወ​ርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መው​ጣት ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡ​አ​ችሁ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ እነሆ” አላ​ቸው።


እነ​ሆም፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከይ​ሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ፥ “መሠ​ዊያ ሆይ፥ መሠ​ዊያ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮ​ስ​ያስ የሚ​ባል ልጅ ለዳ​ዊት ቤት ይወ​ለ​ዳል፤ ዕጣ​ንም የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ብ​ህን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹን ካህ​ናት ይሠ​ዋ​ብ​ሃል፤ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት ያቃ​ጥ​ል​ብ​ሃል” ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጠራ።


ስለ በደ​ለ​ውና እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት እስ​ራ​ኤ​ልን ይጥ​ላል።”


ይኸ​ውም ኢዮ​ር​ብ​ዓም ስለ ሠራው ኀጢ​አት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስላ​ስ​ቈ​ጣ​በት ማስ​ቈ​ጣት ነው።


አንድ ነቢ​ይም ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ መጥቶ፥ “የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር በሚ​መ​ጣው ዓመት ይመ​ጣ​ብ​ሃ​ልና፥ በርታ፤ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ዕወቅ” አለው።


ኢዩ ግን በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በፍ​ጹም ልቡ ይሄድ ዘንድ አል​ተ​ጠ​ነ​ቀ​ቀም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ተው ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም።


ንጉ​ሡም የካ​ህ​ና​ቱን አለቃ ኬል​ቅ​ያ​ስን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም መዓ​ርግ ያሉ​ትን ካህ​ናት በረ​ኞ​ቹ​ንም፥ ለበ​ዓ​ልና ለማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ የተ​ሠ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ያወጡ ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውጭ በቄ​ድ​ሮን ሜዳ አቃ​ጠ​ሉት፤ አመ​ዱ​ንም ወደ ቤቴል ወሰ​ዱት።


የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ጣዖት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ ወደ ቄድ​ሮን ፈፋ አወ​ጣው፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ አቃ​ጠ​ለው፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፥ ትቢ​ያ​ው​ንም በሕ​ዝብ መቃ​ብር ላይ ጨመ​ረው።


ነገር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያሳ​ታ​ቸ​ውን የና​ባ​ጥን ልጅ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ኀጢ​አት ተከ​ተለ፤ እር​ሱ​ንም አል​ተ​ወም።


የም​ና​ሴ​ንና የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም፥ የስ​ም​ዖ​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ከተ​ሞች፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ቦታ እን​ዲሁ አነጻ።


መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሰ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቹ​ንና የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ችም አደ​ቀቀ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የኮ​ረ​ብ​ታ​ዎ​ችን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​አ​ጠፋ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።


እስ​ራ​ኤ​ልን ስለ ኀጢ​አቱ በም​በ​ቀ​ል​በት ቀን የቤ​ቴ​ልን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ደግሞ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ይሰ​በ​ራሉ፤ ወደ ምድ​ርም ይወ​ድ​ቃሉ።


ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​መ​ለ​ሳ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልኩ፤ እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ና​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የበ​ዓ​ሊ​ምን አማ​ል​ክ​ትና የአ​ስ​ጣ​ሮ​ትን ምስ​ሎች አራቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብቻ አመ​ለኩ።


跟着我们:

广告


广告