Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 21:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ምና​ሴም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በቤ​ቱም አጠ​ገብ ባለው በዖዛ አት​ክ​ልት ቦታ ተቀ​በረ፤ ልጁም አሞጽ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ምናሴም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ “የዖዛ አትክልት” በሚባለው በቤተ መንግሥቱ አትክልት ውስጥ ተቀበረ። ልጁ አሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ምናሴ ሞተ፤ በቤተ መንግሥቱ ግቢ “የዑዛ የአትክልት ስፍራ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ምናሴ ሞተ፤ በቤተ መንግሥቱ ግቢ “የዑዛ የአትክልት ስፍራ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቤቱም አጠገብ ባለው በዖዛ አትክልት ተቀበረ፤ ልጁም አሞን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 21:18
13 交叉引用  

አሞ​ጽም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ ሁለት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የዮ​ጥባ ሰው የሐ​ሩስ ልጅ ሚሱ​ላም ነበ​ረች።


በዖ​ዛም የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ባለው መቃ​ብሩ ቀበ​ሩት፤ ልጁም ኢዮ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ልጁ አሞጽ፥ ልጁ ኢዮ​ስ​ያስ።


መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስም​ንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያ​ዝ​ን​ለት ሄደ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ እንጂ በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከቤ​ቱም ጋር መል​ካም ሠር​ቶ​አ​ልና በዳ​ዊት ከተማ ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ጋር ቀበ​ሩት።


ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


አካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አላ​ገ​ቡ​ትም፤ ልጁም ሕዝ​ቅ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ልጆች መቃ​ብር በላ​ይ​ኛው ክፍል ቀበ​ሩት፤ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትም ሁሉ በሞቱ አከ​በ​ሩት። ልጁም ምናሴ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ቍጥሩ ከባ​ሕር አሸዋ የሚ​በ​ልጥ በደ​ልን በድ​ያ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ብዙ ነውና፤ ከበ​ደ​ሌም ብዛት የተ​ነሣ ቀና ብዬ የሰ​ማ​ይን ርዝ​መት አይ ዘንድ አገ​ባቤ አይ​ደ​ለም። ሰው​ነ​ቴን ከኀ​ጢ​አቴ አሳ​ር​ፋት ዘንድ በብ​ረት ቀፎ ደከ​ምሁ፤ በዚ​ህም ደግሞ አላ​ረ​ፍ​ሁም፤ መዓ​ት​ህን አነ​ሣ​ሥ​ቻ​ለ​ሁና፥


በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ሞጽ ልጅ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን በመ​ን​ግ​ሥቱ በዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል መጣ​ለት።


አህ​ያም እን​ደ​ሚ​ቀ​በር ይቀ​በ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በር ወደ ውጭ ተጐ​ትቶ፥ በው​ራጅ ጨርቅ ተጠ​ቅ​ልሎ ይጣ​ላል።”


በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።


ሳሙ​ኤ​ልም ሞተ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ በአ​ር​ማ​ቴ​ምም በቤቱ ቀበ​ሩት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ።


跟着我们:

广告


广告