Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ፈ​ጽ​መው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክቱ ይህ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሂ​ድን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው ይመ​ለስ?” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኢሳይያስም፣ “እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም ምልክቱ ይህ ነው፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይቅደምን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢሳይያስም “እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል የሚፈጽም ስለ መሆኑ ራሱ ምልክት ይሰጥሃል፤ እንግዲህ አሁን የምትመርጠው ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ነው? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኢሳይያስም “እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል የሚፈጽም ስለ መሆኑ ራሱ ምልክት ይሰጥሃል፤ እንግዲህ አሁን የምትመርጠው ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ነው? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢሳይያስም “እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሄድ ዘንድ ወይም ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ ዘንድ ትወድዳለህን?” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 20:9
10 交叉引用  

“ይህም ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በዚህ ዓመት የገ​ቦ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ለህ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ለህ፤ ታጭ​ድ​ማ​ለህ፥ ወይ​ንም ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ለህ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “ጥላው ዐሥር ደረጃ ቢጨ​ምር ቀላል ነገር ነው፤ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመ​ለሰ” አለው።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ፈ​ው​ሰኝ፥ እኔስ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ድ​ወጣ ምል​ክቱ ምን​ድን ነው?” አለው።


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ለሞት እስ​ኪ​ደ​ርስ ታመመ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።


ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገ​ባ​ዖን እነ​ር​ሱን ባጠ​ፋ​በት፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በጠ​ፉ​በት ቀን ኢያሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ተነ​ጋ​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “በገ​ባ​ዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢ​ሎ​ንም ሸለቆ ጨረቃ፤”


ነገር ግን ወደ እኛ ውጡ ቢሉን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና እን​ወ​ጣ​ለን፤ ምል​ክ​ታ​ች​ንም ይህ ይሆ​ናል።”


跟着我们:

广告


广告