Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም የነ​በሩ የነ​ቢ​ያት ልጆች ወደ ኤል​ሳዕ ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ህን ከራ​ስህ ላይ ዛሬ እን​ዲ​ወ​ስ​ደው ዐው​ቀ​ሃ​ልን?” አሉት። እር​ሱም፥ “አዎን፥ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ዝም በሉ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በኢያሪኮ የነበሩትም የነቢያት ማኅበር ወደ ኤልሳዕ ወጥተው፣ “ለመሆኑ እግዚአብሔር፣ ጌታህን ኤልያስን ዛሬ ከአንተ ነጥሎ እንደሚወስደው ዐውቀሃልን?” አሉት። እርሱም፣ “አዎን ዐውቄአለሁ፤ እናንተ ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በዚያም የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው፥ “እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን?” ሲሉ ጠየቁት። ኤልሳዕም “አዎ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚያም የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው፥ “እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን?” ሲሉ ጠየቁት። ኤልሳዕም “አዎ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በኢያሪኮም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ቀርበው “እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው አውቀሃልን?” አሉት። እርሱም “አዎን፥ አውቄአለሁ፤ ዝም በሉ፤” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 2:5
18 交叉引用  

አባ​ቱም እንቢ አለ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አው​ቃ​ለሁ ልጄ ሆይ፥ አው​ቃ​ለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ ታላ​ቅም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወን​ድሙ ከእ​ርሱ ይበ​ል​ጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆ​ናል።”


በቤ​ቴ​ልም የነ​በሩ የነ​ቢ​ያት ልጆች ወደ ኤል​ሳዕ መጥ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ህን ከአ​ንተ ለይቶ ዛሬ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ዐው​ቀ​ሃ​ልን?” አሉት። እር​ሱም፥ “አዎን፥ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ዝም በሉ” አላ​ቸው።


ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች የአ​ንዱ ሚስት የሆ​ነች አን​ዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪ​ያህ ሞቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆ​ቼን ባሪ​ያ​ዎች አድ​ርጎ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው መጥ​ቶ​አል” ብላ ወደ ኤል​ሳዕ ጮኸች።


እር​ሱም፥ “ሁሉ ደኅና ነው፦ አሁን ከነ​ቢ​ያት ወገን የሆኑ ሁለት ጐል​ማ​ሶች ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ወደ እኔ መጥ​ተ​ዋ​ልና፤ አንድ መክ​ሊት ብርና ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ” አለው።


የነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች ኤል​ሳ​ዕን፥ “እነሆ፥ በፊ​ትህ የም​ና​ድ​ር​በት ቤት ጠብ​ቦ​ናል።


ነቢ​ዩም ኤል​ሳዕ ከነ​ቢ​ያት ልጆች አን​ዱን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ይህን የዘ​ይት ቀንድ በእ​ጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድም ሂድ።


ለመ​ቅ​ደድ ጊዜ አለው፥ ለመ​ስ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ና​ገ​ርም ጊዜ አለው፤


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ አለ​ቆች ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት ቀር​በው ፍር​ድን ይና​ገሩ።


አሞ​ጽም መልሶ አሜ​ስ​ያ​ስን አለው፥ “እኔ ላም ጠባ​ቂና በለስ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነ​ቢይ ልጅ አይ​ደ​ለ​ሁም፤


እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።


እየ​ባ​ረ​ካ​ቸ​ውም ራቃ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ይም ዐረገ።


እነ​ር​ሱም፥ “እና​ንተ የገ​ሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየ​አ​ያ​ችሁ ለምን ቆማ​ች​ኋል? ይህ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ያረ​ገው ኢየ​ሱስ፥ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ሲያ​ርግ እን​ዳ​ያ​ች​ሁት እን​ዲሁ ዳግ​መኛ ይመ​ጣል” አሏ​ቸው።


በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የመ​ረ​ጣ​ቸው ሐዋ​ር​ያ​ትን አዝዞ እስከ ዐረ​ገ​ባት ቀን ድረስ ያለ​ውን ጽፌ​ል​ሃ​ለሁ።


ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ክቡር ፊስ​ጦስ ሆይ፥ እው​ነ​ትና የተ​ጣራ ነገ​ርን እና​ገ​ራ​ለሁ እንጂ ዕብ​ደ​ትስ የለ​ብ​ኝም።


ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።


跟着我们:

广告


广告