Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነ​ር​ሱም፥ “እነሆ፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር አምሳ ኀ`ያላን ሰዎች አሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ወይም ወደ አንድ ተራራ ወይም ወደ አንድ ኮረ​ብታ ጥሎት እንደ ሆነ፥ ሄደው ጌታ​ህን ይፈ​ል​ጉት” አሉት። ኤል​ሳ​ዕም፥ “አት​ላኩ፤” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም፣ “እነሆ፤ እኛ አገልጋዮችህ እዚህ ዐምሳ ጠንካራ ሰዎች አሉን፤ ምናልባትም የእግዚአብሔር መንፈስ ጌታህን አንሥቶ ከአንዱ ተራራ ላይ አስቀምጦት ወይም ከአንዱ ሸለቆ አግብቶት ይሆናልና እስኪ ሄደው ይፈልጉት” አሉት። ኤልሳዕም፣ “አይሆንም፤ አትላኳቸው” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “እነሆ! በዚህ ጠንካሮች የሆንን ኀምሳ ሰዎች አለን፤ እንሂድና ጌታህን እንፈልገው፤ ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወስዶ በአንድ ተራራ ላይ ወይም ሸለቆ ውስጥ አሳርፎት ይሆናል።” ኤልሳዕም “አትላኩአቸው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “እነሆ! በዚህ ጠንካሮች የሆንን ኀምሳ ሰዎች አለን፤ እንሂድና ጌታህን እንፈልገው፤ ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወስዶ በአንድ ተራራ ላይ ወይም ሸለቆ ውስጥ አሳርፎት ይሆናል።” ኤልሳዕም “አትላኩአቸው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነርሱም “እነሆ፥ ከባሪያዎችህ ጋር አምሳ ኀያላን ሰዎች አሉ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደ አንድ ተራራ ወይም ወደ አንድ ሸለቆ ጥሎት እንደ ሆነ፥ ሄደው ጌታህን ይፈልጉት ዘንድ እንለምንሃለን፤” አሉት። እርሱም “አትስደዱ” አላቸው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 2:16
8 交叉引用  

እኔም ከአ​ንተ ጥቂት ራቅ ስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አን​ሥቶ ወደ​ማ​ላ​ው​ቀው ስፍራ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ እኔም ገብቼ ለአ​ክ​ዓብ ስና​ገር፥ ባያ​ገ​ኝህ ይገ​ድ​ለ​ኛል፤ እኔም ባሪ​ያህ ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈራ ነበር።


ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች አምሳ ሰዎች ሄዱ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ርቀው ቆሙ፤ እነ​ዚ​ህም ሁለቱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ቆመው ነበር።


መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በራ​እይ ወደ ከላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ወደ ምር​ኮ​ኞቹ አመ​ጣኝ።


መን​ፈ​ስም አን​ሥቶ ወሰ​ደኝ፤ እኔም በም​ሬ​ትና በመ​ን​ፈሴ ሙቀት ሄድሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ በር​ትታ ነበር።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራእይ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር አመ​ጣኝ፤ እጅ​ግም በረ​ዘመ ተራራ ላይ አኖ​ረኝ፤ በዚ​ያም ላይ እንደ ከተማ ሆኖ የተ​ሠራ ነገር በፊቴ ነበረ።


እጅ መሳ​ይ​ንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕ​ሬም ያዘኝ፤ መን​ፈ​ስም በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራእይ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ በር መግ​ቢያ ቅን​አት የተ​ባ​ለው ምስል ወደ አለ​በት አመ​ጣኝ፤


ከው​ኃ​ዉም ከወጡ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፊል​ጶ​ስን ነጥቆ ወሰ​ደው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ዉም ከዚያ ወዲያ አላ​የ​ውም፤ ደስ እያ​ለ​ውም መን​ገ​ዱን ሄደ።


跟着我们:

广告


广告