Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 19:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ስለ እኔም፥ ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊ​ትም ይህ​ችን ከተማ እጋ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ‘ስለ ራሴና ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል፣ ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ፤ አድናታለሁም።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ስለ ራሴ ክብር እንዲሁም ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ይህችን ከተማ እኔ ራሴ ተከላክዬ አድናታለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ስለ ራሴ ክብር እንዲሁም ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ይህችን ከተማ እኔ ራሴ ተከላክዬ አድናታለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ስለ እኔም፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ።’”

参见章节 复制




2 ነገሥት 19:34
21 交叉引用  

ነገር ግን ልጁን ከእ​ርሱ በኋላ ያስ​ነሣ ዘንድ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ያጸና ዘንድ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ዳዊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መብ​ራ​ትን አደ​ረ​ገ​ለት፤


በዕ​ድ​ሜ​ህም ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አን​ተ​ንና ይህ​ችን ከተማ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ እታ​ደ​ጋ​ለሁ፤ ስለ እኔ፥ ስለ ባሪ​ያ​ዬም ስለ ዳዊት ይህ​ችን ከተማ አጋ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”


ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለል​ጆቹ በዘ​መኑ ሁሉ መብ​ራት ይሰ​ጠው ዘንድ ተስፋ እንደ አደ​ረ​ገ​ለት፥ ስለ ባሪ​ያው ስለ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን ያጠፋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።


እን​ደ​ሚ​በ​ርር ወፍ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ይከ​ል​ላ​ታ​ልም፤ ይታ​ደ​ጋ​ታል፤ አል​ፎም ያድ​ና​ታል።


አን​ተ​ንና ይህ​ች​ንም ከተማ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ና​ለሁ፤ ለዚ​ችም ከተማ እቆ​ም​ላ​ታ​ለሁ።


መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።


ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ ይህን ለአ​ንተ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ስሜ ተነ​ቅ​ፎ​አ​ልና፤ ክብ​ሬ​ንም ለሌላ አል​ሰ​ጥም።


ስለ ስሜ ቍጣ​ዬን አሳ​ይ​ሃ​ለሁ፤ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ህም ግር​ማ​ዬን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ።


ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።


በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ነ​ግሥ ልጅ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ለት ከባ​ሪ​ያዬ ከዳ​ዊት ጋር፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈ​ር​ሳል።


እኔም ደግሞ በአ​ብ​ር​ሃ​ምና በይ​ስ​ሐቅ በያ​ዕ​ቆ​ብም ዘር ላይ ገዢ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እን​ዳ​ላ​ስ​ነሣ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንና የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘር እጥ​ላ​ለሁ፤ ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥ እም​ራ​ቸ​ው​ማ​ለ​ሁና።”


“ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በገ​ባ​ች​ሁ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ስላ​ረ​ከ​ሳ​ች​ሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እና​ንተ የም​ሠራ አይ​ደ​ለ​ሁም።


ነገር ግን የይ​ሁ​ዳን ልጆች ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ በቀ​ስት ወይም በሰ​ይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠ​ረ​ገላ፥ ወይም በፈ​ረ​ሶች፥ ወይም በፈ​ረ​ሰ​ኞች የማ​ድ​ና​ቸው አይ​ደ​ለም” አለው።


እኔም ማንም እንዳይሄድና እንዳይመለስ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ በቤቴ ዙሪያ ሰፈር አደርጋለሁ፣ አሁንም በዓይኔ አይቻለሁና ከዚህ በኋላ አስጨናቂ አያልፍባቸውም።


ይኸ​ውም ለጌ​ት​ነቱ ክብር የር​ስ​ታ​ችን መያዣ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ች​ንም ቤዛ​ነት ነው።


በሚ​ወ​ደው ልጁ የሰ​ጠን የጸ​ጋው ክብር ይመ​ሰ​ገን ዘንድ።


ነገር ግን ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ታ​በዩ፦ እጃ​ችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሁሉ አላ​ደ​ረ​ገም እን​ዳ​ይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።


跟着我们:

广告


广告