Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 18:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም አት​ስሙ፤ የአ​ሶር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ፤ ወደ እኔም ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከወ​ይ​ና​ች​ሁና ከበ​ለ​ሳ​ችሁ ብሉ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዳ​ች​ሁም ውኃ ጠጡ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “ሕዝቅያስን አትስሙ። የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፤ ‘ከእኔ ጋራ ተስማሙ፤ ወደ እኔም ውጡ። ከዚያም እያንዳንዳችሁ ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ከከተማችሁ ወጥታችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ አዞአችኋል፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁም እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላና የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጉድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ከከተማችሁ ወጥታችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ አዞአችኋል፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁም እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላና የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሕዝቅያስንም አትስሙ፤’ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል ‘ከእኔ ጋር ታረቁ፤ ወደ እኔም ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፤ ከጕድጓዳችሁም ውሃ ጠጡ፤

参见章节 复制




2 ነገሥት 18:31
10 交叉引用  

እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።”


ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም።


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ባሕር አሸዋ ብዛት ብዙ ነበሩ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም፥ ደስም ይላ​ቸው ነበር።


በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከወ​ይ​ኑና ከበ​ለሱ በታች ተዘ​ል​ለው ይቀ​መጡ ነበር።


እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት፦ በአ​ንተ ፋንታ በዙ​ፋ​ንህ ላይ የማ​ስ​ቀ​ም​ጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል ብሎ እንደ ነገ​ረው፥ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስ​ባ​ለሁ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ር​ግጥ ያድ​ነ​ናል፤ ይህ​ች​ንም ከተማ የአ​ሦር ንጉሥ ሊይ​ዛት አይ​ች​ልም እያለ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ት​ታ​መኑ አያ​ድ​ር​ጋ​ችሁ።


ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።


ታላ​ላ​ቆ​ች​ዋም ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ውኃ ሰደዱ፤ ወደ ጕድ​ጓድ መጡ፤ ውኃም አላ​ገ​ኙም፤ ዕቃ​ቸ​ው​ንም ባዶ​ውን መለሱ፤ ዐፈ​ሩም፤ ተዋ​ረ​ዱም፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።


በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።


跟着我们:

广告


广告