Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ “በድ​ያ​ለሁ፥ ከእኔ ተመ​ለስ፤ የም​ት​ጭ​ን​ብ​ኝ​ንም ሁሉ እሸ​ከ​ማ​ለሁ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ላይ ሦስት መቶ መክ​ሊት ብርና ሠላሳ መክ​ሊት ወርቅ ጫነ​በት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ፣ “በደለኛው እኔ ነኝ፤ ተመለስልኝ፤ እኔም የምትጠይቀኝን ሁሉ እከፍላለሁ፤” ሲል በለኪሶ ወደ ሰፈረው ወደ አሦር ንጉሥ ይህን መልእክት ላከ። የአሦርም ንጉሥ፣ የይሁዳን ንጉሥ ሕዝቅያስን ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ እንዲያገባለት ጠየቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሕዝቅያስም በላኪሽ ሰፍሮ ለነበረው ለሰናክሬም “እኔ በድያለሁ፤ እባክህን አቁም፤ የምትጠይቀኝን ሁሉ እከፍላለሁ” ሲል መልእክት ላከ፤ ንጉሠ ነገሥቱም “እኔ የምፈልገው ዐሥር ሺህ ኪሎ ብርና አንድ ሺህ ኪሎ ወርቅ እንድትልክልኝ ነው” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሕዝቅያስም በላኪሽ ሰፍሮ ለነበረው ለሰናክሬም “እኔ በድያለሁ፤ እባክህን አቁም፤ የምትጠይቀኝን ሁሉ እከፍላለሁ” ሲል መልእክት ላከ፤ ንጉሠ ነገሥቱም “እኔ የምፈልገው ዐሥር ሺህ ኪሎ ብርና አንድ ሺህ ኪሎ ወርቅ እንድትልክልኝ ነው” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የይሁዳም ንጉሥ ሕዝቅያስ “በድያለሁ፤ ከእኔ ተመለስ፤ የምትጭንብኝን ሁሉ እሸከማለሁ፤” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ ጫነበት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 18:14
9 交叉引用  

አክ​ዓ​ብም አዝኖ ሄደ፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ ተኝቶ ፊቱን ተሸ​ፋ​ፈነ፤ እን​ጀ​ራ​ንም አል​በ​ላም።


የአ​ክ​አ​ብም የቤቱ አለ​ቆች፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹና ልጆ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ን​ንም ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ የም​ና​ነ​ግ​ሠው ሰው የለም፤ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አድ​ርግ” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ እር​ሱም ወደ ለኪሶ ኮበ​ለለ፤ ወደ ለኪ​ሶም ተከ​ተ​ሉት፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት።


ምና​ሔ​ምም ብሩን ለአ​ሶር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ባለ​ጠ​ጎች ሁሉ ላይ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስ​ገ​ብሮ አወጣ። የአ​ሶ​ርም ንጉሥ ተመ​ለሰ፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱም አል​ተ​ቀ​መ​ጠም።


በሚ​ሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ በአ​ሦ​ርም ንጉሥ ላይ ዐመፀ፤ አል​ተ​ገ​ዛ​ለ​ት​ምም።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በሎ​ምና ሲዋጋ አገ​ኘው።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የቀ​ሩ​ትን የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ሁሉ፥ ለኪ​ሶ​ንና አዚ​ቃ​ንም ይወጋ ነበር። እነ​ዚህ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች በይ​ሁዳ ከተ​ሞች መካ​ከል ቀር​ተው ነበ​ርና።


ያለ​ዚያ ግን፥ ገና በሩቁ ሳለ አማ​ላ​ጆች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ ዕርቅ ይለ​ም​ናል።


跟着我们:

广告


广告