Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 15:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 በዚ​ያም ወራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሶ​ር​ያን ንጉሥ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ፋቁ​ሔን በይ​ሁዳ ላይ መላክ ጀመረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔን ይሁዳን እንዲወጉ አደረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና፥ የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በይሁዳ ላይ አደጋ እንዲጥሉባት የላካቸው ይኸው ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠበት ዘመን ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና፥ የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በይሁዳ ላይ አደጋ እንዲጥሉባት የላካቸው ይኸው ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠበት ዘመን ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 በዚያም ወራት እግዚአብሔር የሶርያን ንጉሥ ረአሶንንና የሮሜልዩን ልጅ ፋቁሔን በይሁዳ ላይ መስደድ ጀመረ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 15:37
18 交叉引用  

በዚ​ያም ወራት እዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ያጠፋ ጀመረ፤ አዛ​ሄ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ዳርቻ ሁሉ መታ​ቸው።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በአ​ምሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ሃያ ዓመ​ትም ነገሠ።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ታም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ኢዮ​አ​ታ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ ልጁም አካዝ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ያን ጊዜም የሶ​ርያ ንጉሥ ረአ​ሶ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ሊዋጉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ፤ አካ​ዝ​ንም ከበ​ቡት፥ ሊያ​ሸ​ን​ፉት ግን አል​ቻ​ሉም።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በአ​ንድ ቀን ከይ​ሁዳ ጽኑ​ዓን የነ​በሩ መቶ ሃያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞ​ችን ገደለ፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ በአ​ካዝ ዘመን የአ​ራም ንጉሥ ረአ​ሶን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ሊወጉ ወጡ፤ ሊይ​ዙ​አ​ትም አል​ቻ​ሉም።


የአ​ራም ራስ ደማ​ስቆ ነው፤ የደ​ማ​ስ​ቆም ራስ ረአ​ሶን ነው፤ በስ​ድሳ አም​ስት ዓመት ውስጥ የኤ​ፍ​ሬም መን​ግ​ሥት ከሕ​ዝብ ይጠ​ፋል፤


“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችን እል​ካ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ያጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ዋል፤ ከዚ​ያም በኋላ ብዙ አድ​ዳ​ኞ​ችን እል​ካ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ከየ​ተ​ራ​ራ​ውና ከየ​ኮ​ረ​ብ​ታው ሁሉ ከየ​ድ​ን​ጋ​ዩም ስን​ጣቂ ውስጥ ያድ​ድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል።


እነሆ ስሜ የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን ከተማ አስ​ጨ​ን​ቃት ዘንድ እጀ​ም​ራ​ለሁ፤ በውኑ እና​ንተ መን​ጻ​ትን ትነ​ጻ​ላ​ች​ሁን? በም​ድር በሚ​ኖሩ ሁሉ ላይ ሰይ​ፍን እጠ​ራ​ለ​ሁና አት​ነ​ጹም፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪ​ያ​ዬን የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ ዙፋ​ኑ​ንም እኔ በሸ​ሸ​ግ​ኋ​ቸው በእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤ ጋሻ​ዎ​ቹ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ ያነ​ሣል።


ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅ​ን​ታ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አንሡ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ መጥ​ቶ​አ​ልና።”


በራ​ብና በጥ​ማት፥ በዕ​ራ​ቁ​ት​ነ​ትም፥ ሁሉ​ንም በማ​ጣት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ል​ክ​ብህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ትገ​ዛ​ለህ፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ በአ​ን​ገ​ትህ ላይ የብ​ረት ቀን​በር ይጭ​ናል።


በዚ​ያም ቀን በቤቱ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈ​ጽ​ም​በ​ታ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告