Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 15:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰ​ማ​ር​ያም በን​ጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአ​ር​ጎ​ብና ከአ​ርያ ጋር መታው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከጦር አለቆቹ አንዱ የሆነው የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ አሤረበት፤ ዐምሳ የገለዓድ ሰዎች ይዞ በመሄድ፣ ሰማርያ ቤተ መንግሥት ባለው ምሽግ ፋቂስያስን ከአርጎብና ከአርያ ጋራ ገደለው፤ በእግሩም ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከፈቃሕያ ሠራዊት መካከል ፈቁሔ ተብሎ የሚጠራ የረማልያ ልጅ የሆነ አንድ የጦር መኰንን ከኀምሳ የገለዓድ ሰዎች ጋር ሆኖ ሤራ ጠነሰሰ፤ በሰማርያ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ዘልቆ በመግባትም ፈቃሕያን ከአርጎብና ከሃርዬ ጋር ገድሎ በፈቃሕያ እግር ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከፈቃሕያ ሠራዊት መካከል ፈቁሔ ተብሎ የሚጠራ የረማልያ ልጅ የሆነ አንድ የጦር መኰንን ከኀምሳ የገለዓድ ሰዎች ጋር ሆኖ ሤራ ጠነሰሰ፤ በሰማርያ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ዘልቆ በመግባትም ፈቃሕያን ከአርጎብና ከሃርዬ ጋር ገድሎ በፈቃሕያ እግር ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ተማማለበት፤ በሰማርያም በንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአርጎብና ከአርያ ጋር መታው፤ ከእርሱም ጋር አምሳ የገለዓድ ሰዎች ነበሩ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 15:25
10 交叉引用  

ዘም​ሪም ከተ​ማ​ዪቱ እንደ ተያ​ዘች ባየ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ገባ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት በራሱ ላይ በእ​ሳት አቃ​ጠለ፤ ሞተም።


የእ​ኩ​ሌ​ቶቹ ፈረ​ሶች አለቃ ዘም​ሪም አሽ​ከ​ሮ​ቹን ሁሉ ሰብ​ስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴ​ርሳ ነበረ፤ በቴ​ር​ሳም በነ​በ​ረው በመ​ጋ​ቢው በአሳ ቤት ይሰ​ክር ነበር።


የኢ​ያ​ቢ​ስም ልጅ ሴሎም፤ ሌሎ​ችም ከዱት፤ በይ​ብ​ል​ዓም መት​ተው ገደ​ሉት፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ሴሎም ነገሠ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።


የቀ​ረ​ውም የፋ​ቂ​ስ​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


በይ​ሁዳ ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በአ​ምሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ሃያ ዓመ​ትም ነገሠ።


እን​ዲ​ሁም የና​ሜሲ ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዩ ኢዮ​ራ​ምን ከዳው። ኢዮ​ራ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል የተ​ነሣ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድን ይጠ​ብቁ ነበር።


በገ​ባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆች ተቀ​ም​ጠው አገኘ፤ እር​ሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ የም​ና​ገ​ረው መል​እ​ክት አለኝ” አለ። ኢዩም፥ “ከማ​ን​ኛ​ችን ጋር ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ነው” አለ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በአ​ንድ ቀን ከይ​ሁዳ ጽኑ​ዓን የነ​በሩ መቶ ሃያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞ​ችን ገደለ፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ በአ​ካዝ ዘመን የአ​ራም ንጉሥ ረአ​ሶን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ሊወጉ ወጡ፤ ሊይ​ዙ​አ​ትም አል​ቻ​ሉም።


跟着我们:

广告


广告