2 ነገሥት 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 የእግዚአብሔርም ሰው አዝኖ፥ “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መትተኸው ቢሆን ኖሮ ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በመታኻቸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶርያን ትመታለህ” አለ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 የእግዚአብሔርም ሰው ተቈጣውና፣ “መሬቱን ዐምስት ወይም ስድስት ጊዜ መውጋት ነበረብህ፤ እንዲህ ብታደርግ ኖሮ ሶርያን ታሸንፍና ፈጽመህ ትደመስሳት ነበር፤ አሁን ግን የምታሸንፈው ሦስት ጊዜ ብቻ ነው” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ይህም ኤልሳዕን አስቆጣው፤ ስለዚህም ንጉሡን “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መተህ ቢሆን ኖሮ በሶርያውያን ላይ ፍጹም ድልን ትቀዳጅ ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ድል ትነሣቸዋለህ” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ይህም ኤልሳዕን አስቈጣው፤ ስለዚህም ንጉሡን “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መተህ ቢሆን ኖሮ በሶርያውያን ላይ ፍጹም ድልን ትቀዳጅ ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ድል ትነሣቸዋለህ” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የእግዚአብሔርም ሰው ተቆጥቶ “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መትተኸው ቢሆን ኖሮ ሶርያን እስክታጠፋው ድረስ በመታኸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶርያን ትመታለህ፤” አለ። 参见章节 |