Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ካህኑ ዮዳሄ ግን አንድ ሣጥን ወስዶ መክ​ደ​ኛ​ውን ነደ​ለው፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ገ​ባ​በት መግ​ቢያ በስ​ተ​ቀኝ አኖ​ረው፤ ደጁ​ንም የሚ​ጠ​ብቁ ካህ​ናት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​መ​ጣ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ በሚ​ዛን አስ​ገቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀለት፤ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚያስገባው በስተቀኝ በኩል በመሠዊያው አጠገብ አኖረው። በራፉን የሚጠብቁት ካህናትም ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣውን ገንዘብ በሙሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚህ በኋላ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀ፤ ሣጥኑንም ወስዶ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ በስተ ቀኝ በሚገኘው መሠዊያ አጠገብ አኖረው፤ የየዕለቱ ተረኞች የነበሩትም ካህናት ለስግደት የሚመጡት ሰዎች የሚሰጡትን የገንዘብ መባ እየተቀበሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡት ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህ በኋላ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀ፤ ሣጥኑንም ወስዶ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ በስተ ቀኝ በሚገኘው መሠዊያ አጠገብ አኖረው፤ የየዕለቱ ተረኞች የነበሩትም ካህናት ለስግደት የሚመጡት ሰዎች የሚሰጡትን የገንዘብ መባ እየተቀበሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡት ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ካህናቱም “ከሕዝቡ ገንዘቡን አንወስድም፤ በቤቱም ውስጥ የተናዱትን አንጠግንም፤” ብለው እሺ አሉ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 12:9
12 交叉引用  

ካህ​ና​ቱም “ከሕ​ዝቡ ገን​ዘ​ቡን አን​ወ​ስ​ድም፤ በቤ​ቱም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን አን​ጠ​ግ​ንም፥” ብለው ተስ​ማሙ።


“ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬል​ቅዩ ወጥ​ተህ ደጃ​ፉን የሚ​ጠ​ብቁ ከሕ​ዝቡ የሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የገ​ባ​ውን ወርቅ ቍጠር።


ንጉ​ሡም የካ​ህ​ና​ቱን አለቃ ኬል​ቅ​ያ​ስን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም መዓ​ርግ ያሉ​ትን ካህ​ናት በረ​ኞ​ቹ​ንም፥ ለበ​ዓ​ልና ለማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ የተ​ሠ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ያወጡ ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውጭ በቄ​ድ​ሮን ሜዳ አቃ​ጠ​ሉት፤ አመ​ዱ​ንም ወደ ቤቴል ወሰ​ዱት።


የአ​በ​ዛ​ዎ​ችም አለቃ ታላ​ቁን ካህን ሠራ​ያን ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ማርኮ ወሰደ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር በሁ​ለ​ተ​ኛው ተራ የሆ​ኑ​ትን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ዘካ​ር​ያ​ስን፥ ቤንን፥ አዝ​ኤ​ልን፥ ስሜ​ራ​ሞ​ትን፥ ኢያ​ሄ​ልን፥ ኡኒን፥ ኤል​ያ​ብን፥ በና​እ​ያን፥ መዕ​ሤ​ያን፥ መታ​ት​ያን፥ ኤል​ፋ​ይን፥ ሜቄ​ድ​ያን፥ በረ​ኞ​ች​ንም አብ​ዲ​ዶ​ምን፥ ኢያ​ኤ​ል​ንና ዖዝ​ያ​ስን አቆሙ።


ካህ​ና​ቱም ሰበ​ንያ፥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ ናት​ና​ኤል፥ ዓማ​ሣይ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ በና​ያስ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት መለ​ከት ይነፉ ነበር። አብ​ዲ​ዶ​ምና ኢያ​ኤ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት በረ​ኞች ነበሩ።


ይቅ​ር​ታና ቅን​ነት ተገ​ናኙ፤ ጽድ​ቅና ሰላም ተስ​ማሙ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በበ​ረ​ኛው በሰ​ሎም ልጅ በማ​ሴው ጓዳ በላይ ባለው በአ​ለ​ቆቹ ጓዳ አጠ​ገብ ወደ አለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ጎዶ​ልያ ልጅ ወደ ሐና​ንያ ልጆች ጓዳ አገ​ባ​ኋ​ቸው።


የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ታላ​ቅን ካህን ሠራ​ያን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን፥ ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ወሰደ፤


ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር፤


በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ መባ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ገቡ ባለ​ጠ​ጎ​ችን አየ።


跟着我们:

广告


广告