Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 12:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም የኢ​ያ​ሙ​ሃት ልጅ ኢያ​ዜ​ክ​ርና የሳ​ሜር ልጅ ኢያ​ዛ​ብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሜ​ስ​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ገዳዮቹ ሹማምትም የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ነበሩ። እርሱም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አሜስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ባርያዎቹም ተነሥተው ዐመፁበት፥ ወደ ሲላ በሚወርደውም መንገድ በሚሎ ቤት ገደሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ባሪያዎቹም ተነሥተው ዐመፁበት፤ ወደ ሲላ በሚወርደውም መንገድ በሚሎ ቤት ገደሉት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 12:21
12 交叉引用  

ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ።


ከበ​ለ​ዓን ቤት የሆነ የአ​ኪያ ልጅ ባኦስ ዐመ​ፀ​በት፤ ናባ​ጥና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ገባ​ቶ​ንን ከብ​በው ነበ​ርና ባኦስ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ልም ሀገር ባለው በገ​ባ​ቶን ገደ​ለው።


በነ​ጋ​ውም ንጉሡ ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ ንጹ​ሓን ናችሁ፤ እነሆ፥ የጌ​ታ​ዬን ቤት የወ​ነ​ጀ​ልሁ የገ​ደ​ል​ኋ​ቸ​ውም እኔ ነኝ፤ እነ​ዚ​ህ​ንስ ሁሉ የገ​ደለ ማን ነው?


በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ካ​ዝ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አስ በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮ​አ​ካዝ በሰ​ማ​ርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ሰባት ዓመ​ትም ነገሠ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ በዮ​አስ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ነገሠ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ እር​ሱም ወደ ለኪሶ ኮበ​ለለ፤ ወደ ለኪ​ሶም ተከ​ተ​ሉት፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት።


መን​ግ​ሥ​ቱም በእጁ በጸ​ና​ለት ጊዜ አባ​ቱን የገ​ደ​ሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ገደለ።


የኢ​ያ​ቢ​ስም ልጅ ሴሎም፤ ሌሎ​ችም ከዱት፤ በይ​ብ​ል​ዓም መት​ተው ገደ​ሉት፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ሴሎም ነገሠ።


እን​ዲ​ሁም የና​ሜሲ ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዩ ኢዮ​ራ​ምን ከዳው። ኢዮ​ራ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል የተ​ነሣ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድን ይጠ​ብቁ ነበር።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ያን ባየ ጊዜ በአ​ት​ክ​ልት ቤት መን​ገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እር​ሱ​ንም ደግሞ አል​ተ​ወ​ውም” ብሎ ተከ​ተ​ለው። በይ​ብ​ላ​ሄ​ምም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በጋይ አቀ​በት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ወጋው። ወደ መጊ​ዶም ሸሸ፥ በዚ​ያም ሞተ።


ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


跟着我们:

广告


广告