Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እነ​ሆም፥ ንጉ​ሡን እንደ ተለ​መ​ደው በዓ​ምዱ አጠ​ገብ ቆሞ፥ ከን​ጉ​ሡም ጋር መዘ​ም​ራ​ንና መለ​ከ​ተ​ኞች ቆመው አየች፤ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎ​አ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር። ጎቶ​ል​ያም ልብ​ስ​ዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እነሆ፤ በወጉ መሠረት ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ፣ ሹማምቱና መለከት ነፊዎቹ ከአጠገቡ ሆነው አየች። የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ይፈነጥዝ፣ መለከትም ይነፋ ነበር። ጎቶልያም ልብሷን ቀድዳ፣ “ይህ ክሕደት ነው! ክሕደት ነው!” ብላ ጮኸች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየችው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ “ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው! ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየችው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ “ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው! ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነሆም፥ ንጉሡ እንደ ተለመደው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ፥ ከንጉሡም ጋር አለቆችና መለከተኞች ቆመው አየች፤ የአገሩም ሕዝብ ሁል ደስ ብሎአቸው ቀንደ መለከት ይነፉ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።

参见章节 复制




2 ነገሥት 11:14
17 交叉引用  

ሮቤ​ልም ወደ ጕድ​ጓዱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ በአ​ጣው ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ።


ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ው​ንም በየ​አ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው ጭነው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ተመ​ለሱ።


እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን ጠር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በፊቱ እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፦ አዶ​ን​ያስ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ ይላሉ።


ካህ​ኑም ዮዳሄ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን የመቶ አለ​ቆች፥ “ወደ ሰልፉ መካ​ከል አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ት​ንም በሰ​ይፍ ግደ​ሉት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፤ ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና።


ንጉ​ሡም በዓ​ምደ ወርቁ አጠ​ገብ ቆሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይከ​ተሉ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንና ምስ​ክ​ሩ​ንም ሥር​ዐ​ቱ​ንም በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸኑ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በቃል ኪዳን ጸኑ።


በሰ​ሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥ​ነው ልብ​ሳ​ቸ​ውን ወሰዱ፤ በሰ​ገ​ነቱ መውጫ እር​ከን ላይም ከእ​ግሩ በታች አነ​ጠ​ፉት፥ መለ​ከ​ትም እየ​ነፉ፥ “ኢዩ ነግ​ሦ​አል” አሉ።


ኢዮ​ራ​ምም መልሶ ነዳና ሸሸ፤ አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም፥ “አካ​ዝ​ያስ ሆይ፥ ዐመፅ ነው” አለው።


ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ደስታ ሆኖ​አ​ልና እስከ ይሳ​ኮ​ርና እስከ ዛብ​ሎን እስከ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ድረስ ለእ​ርሱ አቅ​ራ​ቢያ የነ​በሩ በአ​ህ​ያና በግ​መል በበ​ቅ​ሎና በበሬ ላይ እን​ጀ​ራና ዱቄት የበ​ለስ ጥፍ​ጥ​ፍና የዘ​ቢብ ዘለላ የወ​ይ​ንም ጠጅ፥ ዘይ​ትም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም፥ ፍየ​ሎ​ች​ንም በብዙ አድ​ር​ገው ያመጡ ነበር።


ንጉ​ሡም በዐ​ምዱ ቆሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ትሎ እን​ዲ​ሄድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንና ምስ​ክ​ሩን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም በፍ​ጹም ልቡና በፍ​ጹም ነፍሱ እን​ዲ​ጠ​ብቅ፥ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የቃል ኪዳን ቃል እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት መው​ረ​ጃም በደ​ረሱ ጊዜ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በሙሉ ስለ አዩት ኀይል ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በታ​ላቅ ቃል ያመ​ሰ​ግ​ኑት ዘንድ ጀመሩ።


跟着我们:

广告


广告