2 ነገሥት 10:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለውን የገለዓድን ሀገር ሁሉ፥ በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የጋድንና የሮቤልን የምናሴንም ሀገር፥ ገለዓድንና ባሳንን መታ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ይኸውም ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን የገለዓድን ምድር ሁሉ ሲሆን፣ ይህም በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለው ከአሮዔር አንሥቶ የጋድን፣ የሮቤልንና የምናሴን አገር ገለዓድንና ባሳንን ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 እርሱም የያዘው ግዛት፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ አሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ፥ የሮቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 እርሱም የያዘው ግዛት፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ ዓሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ፥ የሮቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለውን የገለዓድን አገር ሁሉ፥ በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የጋድንና የሮቤልን የምናሴንም አገር፥ ገለዓድንና ባሳንን መታ። 参见章节 |