Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ለምን ላክህ? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ንጉሡንም፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለመሆኑ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ስለ ራስህ ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክኸው በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነውን? ይህን በማድረግህም ከተኛህበት ዐልጋ ፈጽሞ አትነሣም፤ በርግጥ ትሞታለህ’ ” ብሎ ነገረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቁጠር፥ የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁልህ መልእክተኞች በመላክህ ምክንያት ትሞታለህ እንጂ አትድንም!’” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቊጠር፥ የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁልህ መልእክተኞች በመላክህ ምክንያት ትሞታለህ እንጂ አትድንም!’ ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ኤልያስም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ልከሃልና ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም’” አለው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 1:16
13 交叉引用  

ሚክ​ያ​ስም፥ “በሰ​ላም ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለም” አለ። ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።


እነ​ር​ሱም፥ “አንድ ሰው ሊገ​ና​ኘን መጣና፦ ሂዱ፤ ወደ ላካ​ችሁ ንጉሥ ተመ​ል​ሳ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ የላ​ክህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ስለ​ዚህ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በሉት አለን” አሉት።


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ታመመ፤ ለሞ​ትም ደረሰ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።


ግያ​ዝም ንዕ​ማ​ንን ተከ​ተ​ለው፤ ንዕ​ማ​ንም ዘወር ብሎ ወደ እርሱ ሲሮጥ ባየው ጊዜ ሊገ​ና​ኘው ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ፥ “ሁሉ ደኅና ነውን?” አለው።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሂድ፥ መዳ​ንስ ትድ​ና​ለህ በለው፤ ነገር ግን እን​ዲ​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ይ​ቶ​ኛል” አለው።


ንጉ​ሡም አዛ​ሄ​ልን፥ “ገጸ በረ​ከት በእ​ጅህ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው ተቀ​በ​ለው፤ ከዚ​ህም በሽታ እድን እንደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠይ​ቀው” አለው።


በጽ​ዮን ተራ​ሮች እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ አር​ሞ​ን​ዔ​ምም ጠል ነው፤ በዚያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን ሕይ​ወ​ት​ንም ከዛሬ ጀምሮ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዝ​ዞ​አ​ልና።


ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።


ስለ​ዚህ ንገ​ራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ቶ​ቹን በልቡ የሚ​ያ​ኖር፥ የበ​ደ​ሉ​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊቱ የሚ​ያ​ቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ ቢመጣ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጣዖ​ታቱ ብዛት እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告