Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እርሱ ዘርን ለዘሪ ይሰ​ጣል፤ እህ​ል​ንም ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ያበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ የጽ​ድ​ቃ​ች​ሁ​ንም መከር ያበ​ጃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ለዘሪ ዘርን፣ ለመብላት እንጀራን የሚሰጥ እርሱ የምትዘሩትን አትረፍርፎ ይሰጣችኋል፤ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያበዛላችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለዘሪ ዘርን፥ ለመብላትም እንጀራን የሚሰጥ፥ እርሱ የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል፤ ያበረክትላችሁማል፤ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ለዘሪ ዘርን፥ ለምግብ እንጀራን የሚሰጥ አምላክ የምትዘሩትን ዘር አበርክቶ ይሰጣችኋል፤ የልግሥናችሁንም ፍሬ ያበዛላችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 9:10
16 交叉引用  

እን​ግ​ዲህ እኛ በፊ​ትህ እን​ዳ​ን​ሞት፥ ምድ​ራ​ች​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ፥ እኛ​ንም፥ ምድ​ራ​ች​ን​ንም በእ​ህል ግዛን፤ እኛም ለፈ​ር​ዖን አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ ምድ​ራ​ች​ንም ለእ​ርሱ ትሁን፤ እኛ እን​ድ​ን​ድን፥ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም፥ ምድ​ራ​ች​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ እን​ዘራ ዘንድ ዘር ስጠን።”


ክፉ ሰው የበደልን ሥራ ይሠራል፤ ለጻድቃን ዘር ግን የታመነ ዋጋ አለው።


ይህ ወይም ያ ማና​ቸው እን​ዲ​በ​ቅል ወይም ሁለቱ መል​ካም እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምና በማ​ለዳ ዘር​ህን ዝራ፥ በማ​ታም እጅ​ህን አት​ተው።


ብዙ ዝና​ምና በረዶ ከሰ​ማይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ፥ ምድ​ርን እን​ደ​ሚ​ያ​ረ​ካት፥ ታበ​ቅ​ልና ታፈ​ራም ዘንድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጋት፥ ዘርን ለሚ​ዘራ፥ እህ​ል​ንም ለም​ግብ እን​ደ​ሚ​ሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ፥


ለእ​ና​ንተ ጽድ​ቅን ዝሩ፤ የሕ​ይ​ወት ፍሬን ሰብ​ስቡ፤ የጥ​በ​ብ​ንም ብር​ሃን ለራ​ሳ​ችሁ አብሩ፤ የጽ​ድ​ቃ​ችሁ መከር እስ​ኪ​ደ​ርስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት።


“ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።


ይህቺ የዚህ ሥራ አገ​ል​ግ​ሎት ግዳጅ የም​ት​ፈ​ጽ​መው ለዚህ ለቅ​ዱ​ሳን ችግር መሟ​ላት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ዱ​ሳን ዘን​ድም ደግሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ታበ​ዛ​ለች።


አሳ​ንሶ የሚ​ዘራ ለእ​ርሱ እን​ዲሁ መከሩ ያን​ስ​በ​ታል፤ በብዙ የሚ​ዘራ ግን በብዙ ያመ​ር​ታል።


እርሱ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የሚ​ሰ​ጣ​ችሁ፥ ኀይ​ል​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት ነው?


የብ​ር​ሃን ፍሬው በጎ ሥራና እው​ነት፥ ቅን​ነ​ትም ሁሉ ነውና።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጽ​ድ​ቅን ፍሬ ትሞሉ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤


ይህ​ንም የማ​ነ​ሣ​ሣው ስጦ​ታ​ች​ሁን ፈልጌ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ና​ንተ ላይ የጽ​ድቅ ፍሬ ይበዛ ዘንድ ፈልጌ ነው እንጂ።


ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ፤ ይጨምርም።


እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገ ግን ወንድሞች ሆይ!ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቅቁ፥ እንዳዘዝናችሁም በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን።


跟着我们:

广告


广告