Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስለ​ዚ​ህም እጅግ ያመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋል፤ እንደ ታዘ​ዛ​ች​ሁ​ለት፥ በመ​ፍ​ራ​ትና በመ​ደ​ን​ገ​ጥም እንደ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁት ያስ​ባ​ች​ኋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱም በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደ ተቀበላችሁትና ሁላችሁም እንደ ታዘዛችሁ ሲያስታውስ ለእናንተ ያለው ፍቅር እየበረታ ሄዷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደ ተቀበላችሁት፥ የሁላችሁን መታዘዝ እያሰበ ለእናንተ ያለው ፍቅር እጅግ ጨምሯል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሁላችሁም ታዛዦች እንደ ሆናችሁና በፍርሃትና በመንቀጥቀጥም እንደ ተቀበላችሁት ቲቶ ሲያስታውስ፥ ለእናንተ ያለው ፍቅር በጣም ታላቅ ሆኖአል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስለዚህም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደተቀበላችሁት፥ የሁላችሁን መታዘዝ እያሰበ ፍቅሩ በእናንተ ላይ እጅግ በዝቶአል።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 7:15
23 交叉引用  

ዮሴ​ፍም ታወከ፤ አን​ጀቱ ወን​ድ​ሙን ናፍ​ቆ​ታ​ልና፤ ሊያ​ለ​ቅ​ስም ወደደ፤ ወደ እል​ፍ​ኙም ገብቶ በዚያ አለ​ቀሰ።


ደኅ​ነ​ኛ​ውም ሕፃን የነ​በ​ራት ሴት አን​ጀ​ትዋ ስለ ልጅዋ ታው​ኳ​ልና፥ “ጌታዬ ሆይ! አይ​ደ​ለም፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውን ለእ​ር​ስዋ ስጣት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት” ብላ ለን​ጉሡ ተና​ገ​ረች። ያች​ኛ​ዪቱ ግን፥ “አካ​ፍ​ሉን እንጂ ለእ​ኔም ለእ​ር​ስ​ዋም አይ​ሁን” አለች።


ሦስት ቀንም ሳያ​ልፍ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ሰዎች ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ​ዚህ ነገ​ርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጡ።


ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም መተ​ላ​ለፍ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ቃል የሚ​ፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥ​ዋ​ዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ።


እኔ ባሰ​ብሁ ቍጥር እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ ጻዕ​ርም ሥጋ​ዬን ይይ​ዛል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ር​ሀት ተገዙ፥ በረ​ዓ​ድም ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ልጅ ወን​ድሜ እጁን በቀ​ዳዳ ሰደደ፥ አን​ጀ​ቴም ስለ እርሱ ታወ​ከች።


ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?


ኤፍ​ሬም እንደ ተና​ገረ በእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ቱን ወሰደ፤ ለበ​ዓ​ልም አደ​ረ​ገው፤ ሞተም።


ሴት በም​ት​ወ​ል​ድ​በት ጊዜ ወራቷ ስለ ደረሰ ታዝ​ና​ለች፤ ነገር ግን ልጅ​ዋን ከወ​ለ​ደች በኋላ ስለ ደስ​ታዋ ከዚያ ወዲያ ምጥ​ዋን አታ​ስ​በ​ውም፤ በዓ​ለም ወንድ ልጅን ወል​ዳ​ለ​ችና።


መብ​ራት አም​ጥ​ቶም እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ወደ ውስጥ ሄደና ለጳ​ው​ሎ​ስና ለሲ​ላስ ወድቆ ሰገደ።


እኔም በድ​ካ​ምና በፍ​ር​ሀት፥ በብዙ መን​ቀ​ጥ​ቀ​ጥም መጣሁ።


ስለ​ዚ​ህም በሁሉ ትታ​ዘ​ዙኝ እንደ ሆነ፥ ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ዐውቅ ዘንድ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።


ከእ​ና​ንተ የደ​ረሰ ኀዘን በእኛ የለም፤ ከእ​ኛም በእ​ና​ንተ ላይ የደ​ረሰ ኀዘን የለም፤ ነገር ግን በል​ባ​ችሁ አዝ​ና​ች​ኋል።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም በሥ​ጋ​ችሁ ለሚ​ገ​ዙ​አ​ችሁ ጌቶ​ቻ​ችሁ በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ደ​ን​ገጥ፥ በሰፊ ልብም ለክ​ር​ስ​ቶስ እን​ደ​ም​ት​ገዙ ታዘዙ።


በክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሁላ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይ​ሆን፥ ሳል​ኖ​ርም በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ን​ቀ​ጥ​ቀጥ ሆና​ችሁ ለድ​ኅ​ነ​ታ​ችሁ ሥሩ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መረ​ጣ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንና ወዳ​ጆች፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ርኅ​ራ​ኄን፥ ቸር​ነ​ት​ንና ትሕ​ት​ናን፥ የው​ሀ​ት​ንና ትዕ​ግ​ሥ​ትን ልበ​ሱት።


በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፤ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።


ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?


跟着我们:

广告


广告