Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለ እና​ንተ ለእ​ርሱ በተ​መ​ካ​ሁ​በት ሁሉ አላ​ሳ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእ​ና​ንተ በእ​ው​ነት እንደ ተና​ገ​ርን፥ እን​ደ​ዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትም​ክ​ህ​ታ​ችን እው​ነት ሆነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በእናንተ ላይ ያለኝን ትምክሕት ለርሱ ነግሬው ነበር፤ እናንተም አላሳፈራችሁኝም። ነገር ግን ስንነግራችሁ የነበረው ሁሉ እውነት እንደ ሆነ፣ እንደዚሁም ስለ እናንተ ለቲቶ በትምክሕት የነገርነው እውነት መሆኑ ተረጋግጧል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በእርሱ ፊት ስለ እናንተ በተመካሁበት ነገር አላሳፈራችሁኝም፤ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ የተናገርነው እውነት እንደሆነ ሁሉ፥ እንደዚሁም ትምክህታችን በቲቶ ፊት እውነት ሆነ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በእናንተ የነበረኝን ትምክሕት ለቲቶ ነግሬው ነበር፤ እናንተም አላሳፈራችሁኝም፤ ሁልጊዜ እውነትን እንነግራችሁ ነበር፤ ይህም ስለ እናንተ ለቲቶ የነገርነው ትምክሕት እውነት በመሆኑ ተረጋግጦአል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ለእርሱ በምንም ስለ እናንተ የተመካሁ እንደ ሆነ አላፈርሁምና፥ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ በእውነት እንደ ተናገርን፥ እንደዚህ ደግሞ ትምክህታችን በቲቶ ፊት እውነት ሆነ።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 7:14
12 交叉引用  

እነ​ር​ሱም በእ​ው​ነት ቅዱ​ሳን ይሆኑ ዘንድ ስለ እነ​ርሱ እኔ ራሴን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


እና​ን​ተን ለማ​ነጽ እንጂ፥ እና​ን​ተን ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ጠን ሥል​ጣን እጅግ የተ​መ​ካ​ሁት መመ​ካት ቢኖር አላ​ፍ​ርም።


ልመካ ብሻም አላ​ዋቂ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እው​ነ​ቱን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ስላ​ዩ​ኝና ስለ ሰሙኝ እን​ደ​ም​በ​ልጥ አድ​ር​ገው እን​ዳ​ይ​ጠ​ራ​ጠ​ሩኝ ትቸ​ዋ​ለሁ።


ወን​ድ​ሜን ቲቶን ስላ​ላ​ገ​ኘ​ሁት ለሰ​ው​ነቴ ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ተለ​ይች ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄድሁ።


ስለ​ዚ​ህም ተጽ​ና​ን​ተ​ናል፤ በመ​ጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም ስለ ቲቶ ደስታ አብ​ልጦ ደስ አለን፤ በሁ​ላ​ችሁ ዘንድ ሰው​ነ​ቱን አሳ​ር​ፋ​ች​ኋ​ታ​ልና።


በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ዲሁ ብዙ መወ​ደድ አለኝ፤ ስለ እና​ን​ተም የም​መ​ካ​በት ብዙ ነው፤ መጽ​ና​ና​ት​ንም አገ​ኘሁ፤ ከመ​ከ​ራ​ዬም ሁሉ ይልቅ ደስ​ታዬ በዛ​ልኝ።


ነገር ግን ያዘ​ኑ​ትን የሚ​ያ​ጽ​ናና እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቲቶ መም​ጣት አጽ​ና​ናን።


አሁ​ንም መዋ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ንና እኛም በእ​ና​ንተ የም​ን​መ​ካ​በ​ትን ሥራ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ፊት በግ​ልጥ አሳ​ዩ​አ​ቸው።


ዳግ​መኛ ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣቴ በእኔ ምክ​ን​ያት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ታ​ገ​ኙት ክብር ይበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ።


ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን።


跟着我们:

广告


广告