Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 6:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በክ​ብ​ርና በው​ር​ደት፥ በም​ር​ቃ​ትና በር​ግ​ማን፥ እንደ አሳ​ቾች ስን​ታይ እው​ነ​ተ​ኞች ነን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በክብርና በውርደት፣ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል፤ ደግሞም እውነተኞች ስንሆን ሐሰተኞች ተብለናል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በክብርና በውርደት፥ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል። አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ለክብር ወይም ለውርደት ለመወቀስ ወይም ለመመስገን የተዘጋጀን ነን፤ እውነተኞች ስንሆን፥ አታላዮች ተባልን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 6:8
32 交叉引用  

ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!


ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤


“ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፤’ እንዳለ ትዝ አለን።


መጥተውም “መምህር ሆይ! የሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለን፤ ለቄሳር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? እንስጥን ወይስ አንስጥ?” አሉት።


ሕዝ​ቡም ስለ እርሱ ብዙ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፥ “ደግ ሰው ነው” ያሉ ነበሩ፤ ሌሎች ግን፥ “አይ​ደ​ለም፤ ሕዝ​ቡን ያስ​ታል እንጂ” አሉ።


እነ​ር​ሱም፥ “የመቶ አለቃ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ጻድቅ ሰው ነው፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ወገ​ኖች ሁሉ የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ለት ነው፤ ቅዱስ መል​አክ ተገ​ልጦ አን​ተን ወደ ቤቱ እን​ዲ​ጠ​ራህ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ረ​ው​ንም እን​ዲ​ሰማ አዝ​ዞ​ታል፤” አሉት።


መጥ​ተ​ውም ከከ​ተ​ማ​ቸው እን​ዲ​ወጡ ማለ​ዱ​አ​ቸው።


“እንደ ሕጉም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሐና​ንያ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም የሚ​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።


ይህን ሰው ሲሳ​ደ​ብና ወን​ጀል ሲሠራ፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ በየ​ሀ​ገሩ ሲያ​ውክ፥ ናዝ​ራ​ው​ያን የተ​ባ​ሉት ወገ​ኖች የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ት​ንም ክህ​ደት ሲያ​ስ​ተ​ምር አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል።


ነገር ግን በዚህ ነገር በየ​ስ​ፍ​ራው ሁሉ እን​ዲ​ጣሉ በእኛ ዘንድ ታው​ቋ​ልና የአ​ን​ተን ዐሳብ ደግሞ ከአ​ንተ እን​ሰማ ዘንድ እን​ወ​ድ​ዳ​ለን።”


እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና።


ሕዝ​ቡም እጅግ ያከ​ብ​ሩ​አ​ቸው ነበረ። ከሌ​ሎ​ችም ይቀ​ር​ባ​ቸው ዘንድ አንድ ስን​ኳን የሚ​ደ​ፍር አል​ነ​በ​ረም።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን በመ​ል​ካም የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸ​ውን መን​ፈስ ቅዱ​ስና ጥበብ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ለዚህ ሥራም እን​ሾ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።


በውኑ እና መል​ካም ነገር እና​ገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እና​ድ​ርግ እን​ደ​ም​ንል አስ​መ​ስ​ለው የሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩ​ንና የሚ​ነ​ቅ​ፉን ሰዎች እን​ደ​ሚ​ሰ​ድ​ቡን ነን? ለእ​ነ​ር​ሱስ ቅጣ​ታ​ቸው ተዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም የሚ​ነ​ገ​ረው ቃላ​ችን እው​ነ​ትና ሐሰት አል​ተ​ቀ​ላ​ቀ​ለ​በ​ትም።


እኛ እንደ ደካ​ሞች መስ​ለን እንደ ነበ​ርን፥ ይህን በው​ር​ደት እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ነገር ግን ማንም በሚ​ደ​ፍ​ር​በት እኔ ደግሞ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


እኔ አል​ከ​በ​ድ​ሁ​ባ​ች​ሁም፤ ነገር ግን ምክር ዐዋቂ ሆኜ በመ​ጠ​በብ ወሰ​ድ​ኋ​ችሁ።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።


ልመናችን ከስሕተት ወይም ከርኵሰት ወይም ከተንኰል አልነበረምና፤


በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።


ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፤ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።


አሁ​ንም ተግ​ዳ​ሮ​ቱን ተሸ​ክ​መን፥ ወደ እርሱ ወደ ከተ​ማው ውጭ እን​ውጣ።


ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።


ለድሜጥሮስ ሁሉ ይመሰክሩለታል፤ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም ደግሞ እንመሰክርለታለን፤ ምስክርነታችንም እውነት እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።


እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告