2 ቆሮንቶስ 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ሕግ አገልጋዮች አደረገን፤ ፊደል ይገድላል፥ መንፈስ ግን ሕያው ያደርጋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እርሱም በፊደል ላይ ሳይሆን በመንፈስ ላይ የተመሠረተውን የአዲሱ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አደረገን፤ ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ላልሆነ፥ ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን አበቃን፤ ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የሐዲስ ኪዳኑ አገልጋዮች እንድንሆን ብቃትን የሰጠን እርሱ ነው፤ ይህም በፊደል በተጻፈው ሕግ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ነው፤ በፊደል የተጻፈው ሕግ ሞትን ያመጣል፤ መንፈስ ቅዱስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። 参见章节 |