Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነሆ እና​ንተ ስላ​ገ​በ​ራ​ች​ሁኝ በመ​መ​ካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእ​ኔማ በእ​ና​ንተ ዘንድ ልከ​ብ​ርና እና​ን​ተም ምስ​ክ​ሮች ልት​ሆ​ኑኝ ይገ​ባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢም​ንት ብሆ​ንም ዋና​ዎቹ ሐዋ​ር​ያት ሁሉ ከሠ​ሩት ሥራ ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለ​ምና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በመመካቴ ሞኝ ሆኛለሁ፤ ለዚህም ያበቃችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ ስለ እኔ መመስከር የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ። ደግሞም እኔ ከምንም የማልቈጠር ብሆንም፣ “ታላላቅ ሐዋርያት” ከሚባሉት በምንም አላንስም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንደ ሞኝ ተናገርኩ! ታዲያ፥ እንዲህ እንድናገር ያደረጋችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እኔን ማመስገን የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ፤ እኔ ማንነቴ ያልታወቀ ሰው ብሆንም እንኳ ታላላቅ ከተባሉት ሐዋርያት በምንም አላንስም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ፤ እናንተ ግድ አላችሁኝ፤ እናንተ እኔን ልታመሰግኑ ይገባ ነበርና። እኔ ምንም ባልሆን እንኳ፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አልጎድልምና።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 12:11
17 交叉引用  

እን​ዲሁ እና​ን​ተም ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ር​ጋ​ችሁ ‘እኛ ሥራ ፈቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ነን፤ ለመ​ሥ​ራ​ትም የሚ​ገ​ባ​ንን ሠራን’ በሉ።”


ትን​ቢት ብና​ገር፥ የተ​ሰ​ው​ረ​ውን ሁሉ፥ ጥበ​ብ​ንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍ​ለስ የሚ​ያ​ደ​ርስ ፍጹም እም​ነ​ትም ቢኖ​ረኝ ፍቅር ከሌ​ለኝ ከንቱ ነኝ።


ጳው​ሎ​ስም ቢሆን፥ አጵ​ሎ​ስም ቢሆን፥ ጴጥ​ሮ​ስም ቢሆን፥ ዓለ​ምም ቢሆን፥ ሕይ​ወ​ትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ ያለ​ውም ቢሆን፥ የሚ​መ​ጣ​ውም ቢሆን ሁሉ የእ​ና​ንተ ነው።


መከራ ብን​ቀ​በ​ልም እና​ንተ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ጽ​ናኑ ነው፤ ብን​ጽ​ና​ናም እኛ የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ያን መከራ በመ​ታ​ገሥ ስለ​ሚ​ደ​ረግ መጽ​ና​ና​ታ​ችሁ ነው።


በስ​ን​ፍ​ናዬ እና​ገር ዘንድ ጥቂት ልት​ታ​ገ​ሡኝ ይገባ ነበር፤ ቢሆ​ንም በር​ግጥ ታገ​ሡኝ፤


እኔ ግን ሌሎች ሐዋ​ር​ያት ከአ​ስ​ተ​ማ​ሩት ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለም ይመ​ስ​ለ​ኛል።


የሐ​ዋ​ር​ያት ምል​ክ​ትስ በፍ​ጹም ትዕ​ግ​ሥ​ትና በተ​አ​ም​ራት፥ ድንቅ ሥራ በመ​ሥ​ራ​ትና በኀ​ይ​ላት ተደ​ር​ጎ​ላ​ች​ኋል።


ልመካ ብሻም አላ​ዋቂ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እው​ነ​ቱን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ስላ​ዩ​ኝና ስለ ሰሙኝ እን​ደ​ም​በ​ልጥ አድ​ር​ገው እን​ዳ​ይ​ጠ​ራ​ጠ​ሩኝ ትቸ​ዋ​ለሁ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አሁን ደግሞ ራሳ​ች​ንን እያ​መ​ሰ​ገን ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ጀ​ም​ራ​ለ​ንን? ወይስ እንደ ሌሎች ስለ እኛ ወደ እና​ንተ ደብ​ዳቤ እን​ዲ​ጽ​ፉ​ላ​ችሁ፥ ወይስ እና​ንተ ትጽ​ፉ​ልን ዘንድ የም​ን​ሻው አለን?


እኛ ሰነ​ፎች ብን​ሆ​ንም፥ ስን​ፍ​ና​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ዐዋ​ቂ​ዎች ብን​ሆ​ንም ዐዋ​ቂ​ነ​ታ​ችን ለእ​ና​ንተ ነው።


አን​ዱም ምንም ሳይ​ሆን ምንም የሆነ ቢመ​ስ​ለው ራሱን ያታ​ል​ላ​ልና።


ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ለማ​ንስ ለእኔ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ባለ​ጸ​ግ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ አስ​ተ​ምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።


跟着我们:

广告


广告