Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 11:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ነገር ግን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትም ቢሆን፥ የማ​ደ​ር​ገ​ውም ቢሆን፥ እነ​ርሱ እንደ እኛ የሚ​መ​ኩ​በ​ትን ያገኙ ዘንድ፥ ምክ​ን​ያት የሚ​ሹ​ትን ምክ​ን​ያት አሳ​ጣ​ቸው ዘንድ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከእኛ ጋራ እኩል ለመሆን በሥራቸው እየተመኩ ቀን የሚጠብቁትን ሰዎች ምክንያት ለማሳጣት አሁን የማደርገውን ወደ ፊትም አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ነገር ግን በሚመኩበት ሥራ ከእኛ እኩል በአቻነት ለመቆጠር የሚፈልጉ ሰዎችን ምክንያት ለማሳጣት፥ አሁን የማደርገውን ወደፊትም እገፋበታለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እነዚያ ሌሎች ሐዋርያት “እኛም እንደ እነርሱ እንሠራለን” እያሉ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የማደርገውን ወደፊትም ደግሞ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ነገር ግን በዚያ በሚመኩበት እንደ እኛ ሆነው ሊገኙ፥ ምክንያትን ከሚፈልጉቱ ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ አሁን የማደርገውን ከዚህ ወዲህ ደግሞ አደርጋለሁ።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 11:12
13 交叉引用  

“ስለ ፍርድ የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እርሱ የወ​ደ​ደ​ውን ያደ​ር​ጋ​ልና።


ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።


እን​ግ​ዲ​ያስ መታ​በ​ያ​ችሁ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጥቂቱ እርሾ ብዙ​ውን ሊጥ እን​ደ​ሚ​ያ​መጥ አታ​ው​ቁ​ምን?


በእኛ ሹመት ሌላ የሚ​ቀ​ድ​መን ከሆነ የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ይህን አል​ፈ​ለ​ግ​ሁ​ትም፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ትም​ህ​ርት እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል በሁሉ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።


እን​ግ​ዲህ ይህን የመ​ከ​ርሁ በውኑ የሠ​ራ​ሁት እንደ አላ​ዋቂ ሰው ሆኜ ነውን? ወይስ በእኔ በኩል አዎን አዎን፥ አይ​ደ​ለም አይ​ደ​ለም ማለት እን​ዲ​ሆን ያን የም​መ​ክ​ረው ለሰው ይም​ሰል ነውን?


“የሚ​መካ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመካ።”


በሥ​ጋዊ ሥር​ዐት የሚ​መኩ ብዙ​ዎች ናቸ​ውና እኔ ደግሞ እመ​ካ​ለሁ።


ከእ​ና​ንተ ዘንድ በነ​በ​ር​ሁ​በት ጊዜም፥ ስቸ​ገር ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። ባል​በ​ቃ​ኝም ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከመ​ቄ​ዶ​ንያ መጥ​ተው አሙ​አ​ሉ​ልኝ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ እን​ዳ​ል​ከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ በሁሉ ተጠ​ነ​ቀ​ቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለሁ።


በዚህ ደግሞ በእ​ና​ንተ ዘንድ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እኛ እን​ደ​ም​ን​መ​ካ​ባ​ችሁ፥ እና​ን​ተም በእኛ እን​ድ​ት​መኩ፥ ከልብ ሳይ​ሆን ለሰው ይም​ሰል በሚ​መኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እን​ዲ​ሆ​ና​ችሁ ምክ​ን​ያ​ትን እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን።


እርሱ ግን ሌላ አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ያ​ው​ኳ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ሊያ​ጣ​ምሙ የሚ​ወዱ አሉ እንጂ።


እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤


跟着我们:

广告


广告