2 ቆሮንቶስ 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ልብ ሁሉ ይማረክ ዘንድ ኅሊናም ለክርስቶስ ይገዛ ዘንድ በእግዚአብሔር ላይ የሚታበየውንና ከፍ ከፍ የሚለውን እናፈርሳለን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ክርክርና ማንኛውም የእብሪት እንቅፋት እናፈርሳለን፤ አእምሮን ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እግዚአብሔርን በማወቅ ላይ እንቅፋት ሆነው የሚነሡትን ክርክርና ትዕቢት እናፈርሳለን፤ የሰውን ሐሳብ ሁሉ እየማረክንም ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ 参见章节 |