Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ስለ እና​ንተ ያለን ተስ​ፋም የጸና ነው፤ መከ​ራ​ች​ንን እንደ ተካ​ፈ​ላ​ችሁ መጠን፥ እን​ዲሁ በመ​ጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም እን​ደ​ም​ት​ተ​ባ​በሩ እና​ው​ቃ​ለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለ እናንተ ያለን ተስፋ ጽኑ ነው፤ ምክንያቱም በመከራችን እንደ ተካፈላችሁ ሁሉ በመጽናናታችንም እንደምትካፈሉ እናውቃለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሥቃያችንን እንደ ተካፈላችሁ እንዲሁም መጽናናታችንን ደግሞ እንደምትካፈሉ እናውቃለንና፥ ተስፋችን ስለ እናንተ ጽኑ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 መከራችንን በምትካፈሉበት መጠን መጽናናታችንንም እንደምትካፈሉ ስለምናውቅ በእናንተ ላይ ያለን ተስፋ ጽኑ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ተስፋችንም ስለ እናንተ ጽኑ ነው፤ ሥቃያችንን እንደ ተካፈላችሁ እንዲሁም መጽናናታችንን ደግሞ እንድትካፈሉ እናውቃለንና።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 1:7
16 交叉引用  

‘በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር፤’ ስለምትሉ፥ ወዮላችሁ።


በሰው ላይ እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ሰው ያለ ፈተና ነው እንጂ ሌላ ፈተና አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም። በም​ት​ች​ሉት መከራ ነው እንጂ በማ​ት​ች​ሉት መከራ ትፈ​ተኑ ዘንድ ያል​ተ​ዋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ እር​ሱም ከፈ​ተና ትድኑ ዘንድ በመ​ከራ ጊዜ ይረ​ዳ​ች​ኋል።


እኛ መመ​ኪ​ያ​ችሁ እን​ደ​ሆን፥ እን​ዲሁ እና​ን​ተም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን መመ​ኪ​ያ​ችን እን​ድ​ት​ሆኑ በከ​ፊል እን​ዳ​ወ​ቃ​ችሁ ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


ነገር ግን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እን​ደ​ም​ወ​ደው ሆና​ችሁ ያላ​ገ​ኘ​ኋ​ችሁ እንደ ሆነ፤ እኔም እን​ደ​ማ​ት​ወ​ዱት እሆ​ን​ባ​ች​ኋ​ለሁ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ፤ ወይም እኮ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ክር​ክር፥ ኵራት፥ መቀ​ና​ናት፥ መበ​ሳ​ጨት፥ መዘ​ባ​በት፥ ወይም መተ​ማ​ማት፥ መታ​ወክ፥ ወይም ልብን ማስ​ታ​በይ ይኖር ይሆ​ናል።


አሁን ግን እኔ ስለ እርሷ በብዙ ደስ ይለ​ኛል፤ ደስ​ታ​ዬም ስለ አዘ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ንስሓ ልት​ገቡ ስለ አዘ​ና​ችሁ እንጂ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ ስንኳ እን​ዳ​ይ​ጠፋ፥ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብላ​ችሁ አዝ​ና​ች​ኋ​ልና።


ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤


ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።


በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።


እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።


跟着我们:

广告


广告