Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 1:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም የሚ​ነ​ገ​ረው ቃላ​ችን እው​ነ​ትና ሐሰት አል​ተ​ቀ​ላ​ቀ​ለ​በ​ትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔር ታማኝ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ለእናንተ የምንናገረው ቃላችን፣ “አዎን” እና “አይደለም” ሊሆን አይችልም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እግዚአብሔር የታመነ የሆነውን ያህል በእርግጥ እኛ ለእናንተ የምንናገረው ቃል “አዎን” እና “አይደለም” አይሆንም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር ታማኝ ስለ ሆነ እኛም የምንነግራችሁ “አዎን ወይም አይደለም” የሚል የማወላወል ቃል አይደለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔር ግን የታመነ ነው፥ ለእናንተም የሚነገረው ቃላችን አዎንና አይደለም አይሆንም።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 1:18
10 交叉引用  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ምር ቃሉን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እኔን ታው​ቁ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ራሴ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት የላ​ከኝ እው​ነ​ተኛ አለ።


ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውና የም​ፈ​ር​ደው ብዙ አለኝ፤ የላ​ከ​ኝም እው​ነ​ተኛ ነው፤ እኔ በእ​ርሱ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ለዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።”


ከልጁ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የጠ​ራ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው።


እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ የሆነ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሰት እን​ደ​ማ​ል​ና​ገር ያው​ቃል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በሌላ ቀላ​ቅ​ለው እን​ደ​ሚ​ሸ​ቅጡ እንደ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምና፤ በቅ​ን​ነት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተላከ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ና​ገ​ራ​ለን።


በክ​ብ​ርና በው​ር​ደት፥ በም​ር​ቃ​ትና በር​ግ​ማን፥ እንደ አሳ​ቾች ስን​ታይ እው​ነ​ተ​ኞች ነን።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


“በሎዲቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦


“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦


跟着我们:

广告


广告