2 ቆሮንቶስ 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እንግዲህ ይህን የመከርሁ በውኑ የሠራሁት እንደ አላዋቂ ሰው ሆኜ ነውን? ወይስ በእኔ በኩል አዎን አዎን፥ አይደለም አይደለም ማለት እንዲሆን ያን የምመክረው ለሰው ይምሰል ነውን? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ይህን ሳቅድ በሚገባ ሳላስብ ያደረግሁት ይመስላችኋልን? ወይስ በዓለማዊ ልማድ አንዴ፣ “አዎን፣ አዎን” ወዲያው ደግሞ፣ “አይደለም፣ አይደለም” የምል ይመስላችኋልን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ይህን ማድረግ በመፈለጌ የተከፈለ ሐሳብ አሳይቼ ይሆን? ወይስ በእኔ ዘንድ “አዎን፥ አዎን” እና “አይደለም፥ አይደለም” ማለት እንዲሁ በሰብአዊ መመዘኛ በልማድ ይሆን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ይህን ባቀድኩ ጊዜ የማደርገውን የማላውቅ ወላዋይ የሆንኩ ይመስላችኋል? ወይስ ይህን በማቀዴ በአንድ ጊዜ “አዎንና አይደለም” እያልኩ በማወላወል በሰው አስተሳሰብ ያደረግኹት ይመስላችኋልን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እንግዲህ ይህን ሳስብ ያን ጊዜ ቅሌትን አሳየሁን? ወይስ በእኔ ዘንድ አዎን አዎን አይደለም አይደለም ማለት እንዲሆን ያን የማስበው በዓለማዊ ልማድ ነውን? 参见章节 |