2 ዜና መዋዕል 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እኔ ግን መጥቼ በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኩሌታ አልነገሩኝም፤ በሀገሬ ከሰማሁትም ዝና ይልቅ ጨመርህልኝ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ይሁን እንጂ መጥቼ የነገሩኝን በዐይኔ እስካይ ድረስ አላመንሁም ነበር፤ በርግጥም የጥበብህ ታላቅነት እኩሌታው እንኳ አልተነገረኝም፤ እኔ ከሰማሁት ዝና እጅግ ይልቃል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እኔ ግን መጥቼ በዓይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኩሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ይሁን እንጂ እዚህ መጥቼ ሁሉን ነገር በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ ታዲያ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አልሆነም፤ በእርግጥም ጥበብህ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እኔ ግን መጥቼ በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኵሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ። 参见章节 |