Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 9:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ገጸ በረ​ከ​ቱን፥ የወ​ር​ቅ​ንና የብ​ርን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንና የጦር መሣ​ሪ​ያን፥ ሽቱ​ው​ንም፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ዎ​ችን እየ​ያዘ በየ​ዓ​መቱ ያመጣ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በየዓመቱም የሚመጣው ሰው ሁሉ የብርና የወርቅ ዕቃ፣ ልብስ፣ የጦር መሣሪያ፣ ቅመማ ቅመም፣ ፈረስና በቅሎ ስጦታ አድርጎ ያመጣለት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እያንዳንዱም ገጸ በረከቱን፥ የወርቅንና የብርን ዕቃ፥ ልብስንና የጦር መሣሪያን፥ ሽቶውንም፥ ፈረሶችንና በቅሎችን እየያዘ በየዓመቱ ያመጣ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ወደ እርሱም የሚመጡት ሁሉ የብርና የወርቅ፥ የልብስ፥ የጦር መሣሪያዎች፥ የሽቶ፥ የፈረሶችና የበቅሎዎች ስጦታዎችን ያመጡለት ነበር፤ ይህም በየዓመቱ የሚደረግ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እያንዳንዱም ገጸ በረከቱን፥ የወርቅንና የብርን ዕቃ፥ ልብስንና የጦር መሣሪያን፥ ሽቱውንም፥ ፈረሶችንና በቅሎችን እየያዘ በየዓመቱ ያመጣ ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 9:24
11 交叉引用  

ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ እጅ​ግም ብዙ ሽቶ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳባ ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አል​መ​ጣም ነበር።


እነ​ር​ሱም ሁሉ በዓ​መት በዓ​መቱ ገጸ በረ​ከ​ቱን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ፥ ልብ​ስና የጦር መሣ​ሪያ፥ ሽቱም፥ ፈረ​ሶ​ችና በቅ​ሎ​ዎች እየ​ያዙ ይመጡ ነበር።


ኪራ​ምም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ለሰ​ሎ​ሞን አመጣ።


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ እጅ መን​ሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንም ደግሞ ከመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎ​ች​ንና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየ​ሎ​ችን ያመ​ጡ​ለት ነበር።


የም​ድ​ርም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በልቡ ያኖ​ረ​ውን ጥበ​ቡን ይሰሙ ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር።


ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ፥ እጅ​ግም ብዙ ሽቱ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳ​ባም ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ ሽቱ ከቶ አል​ነ​በ​ረም።


ወን​ድ​ሞ​ቹና እኅ​ቶቹ ቀድ​ሞም ያው​ቁት የነ​በ​ሩት ሁሉ የሆ​ነ​ውን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር እን​ጀራ በሉ፥ ጠጡም፤ አጽ​ና​ኑ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባመ​ጣ​በት ክፉ ነገር ሁሉ አደ​ነቁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ጥማድ በሬ፥ አራት ድራ​ህማ የሚ​መ​ዝን ወር​ቅና ብር ሰጡት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በዝ​ማሬ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ በም​ስ​ጋ​ናም ከፍ ከፍ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ማ​ዊ​ውን የጌ​ራን ልጅ ናዖ​ድን ሁለቱ እጆቹ ቀኝ የሆ​ኑ​ለ​ትን ሰው አዳኝ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግ​ሎም እጅ መንሻ ላኩ።


ክፉ​ዎች ሰዎች ግን፥ “ያድ​ነን ዘንድ ይህ ሰው ማን ነው?” ብለው ናቁት፤ እጅ መን​ሻም አላ​መ​ጡ​ለ​ትም።


跟着我们:

广告


广告