Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀድሶ፥ ሰባት ቀን በዓል አድ​ርጎ ነበ​ርና በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የፍ​ጻሜ በዓል አደ​ረገ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 መሠዊያውን ለሰባት ቀን ስለ ቀደሱና የሰባት ቀን በዓል በተጨማሪ ስላከበሩ፣ በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አደረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 መሠዊያውን ለእግዚአብሔር የተለየ በማድረግ ሥነ ሥርዓት ላይ ሰባት ቀን አሳለፉ፤ ሌላ ሰባት ቀን በዓሉን በማክበር ከሰነበቱ በኋላ በስምንተኛው ቀን የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ተደርጎ የበዓሉ ፍጻሜ ሆነ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 7:9
10 交叉引用  

ይኸ​ውም አታ​ሚን በሚ​ባል በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ነበር።


በዚ​ያም ዘመን ሰሎ​ሞን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠ​ራው ቤት ውስጥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፥ ደስ​ታም እያ​ደ​ረጉ ሰባት ቀን በዓ​ሉን አከ​በሩ።


ጉባ​ኤው ሁሉ እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል ያደ​ርጉ ዘንድ ተማ​ከሩ፤ በደ​ስ​ታም እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ቀን ሕዝ​ቡን ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው አሰ​ና​በተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊ​ትና ለሰ​ሎ​ሞን፥ ለሕ​ዝ​ቡም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት በል​ባ​ቸው ደስ ብሎ​አ​ቸው ሄዱ።


ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨ​ረ​ሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ መጽ​ሐፍ ያነ​ብብ ነበር። በዓ​ሉ​ንም ሰባት ቀን ያህል አደ​ረጉ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እንደ ሕጋ​ቸው ወጡ።


ሰባት ቀን መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


ጾምን ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንና በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሰብ​ስቡ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ጩኹ።


ሰባት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ ስም​ን​ተ​ኛ​ዋም ቀን የተ​ቀ​ደ​ሰች ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ የመ​ሰ​ና​በቻ በዓል ነውና፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።


መሠ​ዊ​ያ​ውም በተ​ቀባ ቀን አለ​ቆቹ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ ቍር​ባ​ንን አቀ​ረቡ፤ አለ​ቆ​ችም መባ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት አቀ​ረቡ።


ስድ​ስት ቀን ቂጣ እን​ጀራ ብላ፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን መው​ጫው ስለ​ሆነ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ይሁን፤ ለነ​ፍ​ስም ከሚ​ሠ​ራው በቀር ሥራን ሁሉ አታ​ድ​ር​ግ​በት።


跟着我们:

广告


广告