Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በዚ​ያ​ችም ዕለት ንጉሡ ሰሎ​ሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን ሠዋ። እን​ዲሁ ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቅዳሴ አከ​በሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ንጉሥ ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል ሠዋ፤ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ንጉሡም ሰሎሞን ሀያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሀያ ሺህ በጎች ሠዋ። እንዲሁ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የጌታን ቤት ቀደሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዐይነት ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ንጉሡም ሰሎሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች ሠዋ። እንዲሁ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 7:5
16 交叉引用  

በነ​ጋ​ውም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረበ፤ አንድ ሺህ ወይ​ፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦ​ቶች፥ የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንም፥ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ብዙ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።


ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ን​ኳኑ አጠ​ገብ ወዳ​ለው ወደ ናሱ መሠ​ዊያ ወጣ፤ በዚ​ያም አንድ ሺህ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።


በዚ​ያም ቀን ካመ​ጡት ምርኮ ሰባት መቶ በሬ​ዎ​ች​ንና ሰባት ሺህ በጎ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠዋ።


እነሆ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ታዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የጣ​ፋ​ጩን ሽቱ ዕጣን ለማ​ጠን፥ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት ለማ​ኖር፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በጥ​ዋ​ትና በማታ፥ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ለማ​ቅ​ረብ እኔ ልጁ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠ​ራ​ለሁ፤ እር​ሱ​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ስለ ቍር​ባን ሺህ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ሰባት ሺህ በጎ​ችን ለይ​ሁ​ዳና ለጉ​ባ​ኤው ሰጥቶ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ሺህ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ዐሥር ሺህ በጎ​ችን ለጉ​ባ​ኤው ሰጥ​ተው ነበር፤ ከካ​ህ​ናቱ እጅግ ብዙ ተቀ​ድ​ሰው ነበ​ርና።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት በታ​ቦቷ ፊት ሆነው ከብ​ዛት የተ​ነሣ የማ​ይ​ቈ​ጠ​ሩ​ት​ንና የማ​ይ​መ​ጠ​ኑ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ይሠዉ ነበር።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ነበር።


ካህ​ና​ቱም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ኑም ደግሞ፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ለ​ውን የዳ​ዊ​ትን መዝ​ሙር እየ​ዘ​መሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገን የሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህ​ና​ቱም በፊ​ታ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ቆመው ነበር።


በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ውም፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን መስ​ጠት በአ​ለ​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ እርሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።”


እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?


መሠ​ዊ​ያ​ውም በተ​ቀባ ቀን አለ​ቆቹ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ ቍር​ባ​ንን አቀ​ረቡ፤ አለ​ቆ​ችም መባ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት አቀ​ረቡ።


በዚ​ያም ወራት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የመ​ቅ​ደስ መታ​ደስ በዓል ሆነ፤ ክረ​ም​ትም ነበር።


跟着我们:

广告


广告